Logo
Getu Temesgen
የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
‎
‎#ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት እና ከኔዘርላንድስ ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያዘጋጀው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ሊካሄድ መሆኑን ተገለጸ።
‎
‎ምክር ቤቱ ዘላቂ የሥነ-ምህዳር እንቅስቃሴዎችን ታሳቢ ያደረጉ የንግድና የኢንቨስትመንት ስራዎች በግል ዘርፉ ውስጥ እንዲስፋፉና ተግባራዊ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አስታውሷል።
‎
‎ፖሊሲ አውጪዎች የንግድ ምክር ቤቶችና የዘርፉ አመራሮች የዓለም አቀፍ ተቋማትና የልማት አጋሮች የውጭምና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የፋይናንስ ተቋማትና የቴክኖሎጂ አበጋዞች በአንድ መድረክ ተገናኝተው በአረንጓዴ የንግድ ዘርፍ ምቹ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ዙሪያ ይመክራሉ።
‎
‎በፎረሙ ላይ ዘላቂ ልማትን፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚን፣ የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን፣ የካርቦን ቅነሳን የአካባቢ ጥበቃን እና አረንጓዴ ፋይናንስን የሚመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ይቀርባሉ ተብሏል።
‎
‎በአረንጓዴ ቢዝነስ ዘርፍ ውጤታማ የሆኑ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን አገልግሎቶቻቸውንና ስኬታማ ልምዶቻቸውን ለጎብኚዎችና ለባለሀብቶች ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
‎
‎በዘርፉ የሚሰሩ ባለሀብቶች የፋይናንስ ተቋማትና ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትስስር የሚፈጥሩበትና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ሸሪኮችን የሚያገኙበት ዕድል መመቻቸቱ ተገልጿል።
‎
‎በተለይም አዲስ ቻምበር ከSNV ጋር በመተባበር ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት የንግድ ድጋፍ አገልግሎት፣ የገበያ ትስስር እና የፖሊሲ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሰራ ይገኛል።
‎
‎ይህ ዝግጅት ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ለማፋጠን፣ የዘላቂ ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋፋት እና የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
‎
በጌትነት ተመስገን

‎#greeninvestmentethiopia ​#greenforum2026​#addischamber ​#greeneconomyethiopia
​#sustainableinvestment #gizethiopia
​#snvethiopia #renewableenergyethiopia

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.