(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር የቦንድ ግዢ ዕቅዱን ማሳወቁን ተከትሎ የዶላር አቅም መዳከሙ፣ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች አዳዲስ የትርፍ አማራጮችን ፍለጋ ፊታቸውን ወደ ታዳጊ ገበያዎች እንዲያዞሩ እያደረጋቸው መሆኑን የኢኮኖሚ ትንታኔዎች አመለከቱ። ባለፈው ወር የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት የዋጋ ንረትን እና የዕዳ ጫናን ለማርገብ በማሰብ፣ የረዥም ጊዜ የመንግስት የዕዳ ሰነዶችን (ቦንዶችን) መልሶ የመግዛት ዕቅድን በእጥፍ ማሳደጋቸው ይታወሳል።
በብሩኪንግስ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሮቢን ብሩክስ እንዳሉት ታዳጊ ገበያዎች በቀጣይነት ከፍተኛ የሆነ "የገንዘብ ጎርፍ" ያስተናግዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ታላላቅ ያደጉ ሀገራት የመንግስት ቦንድ ወለድን ለመቀነስ የሚያደርጉት ጥረት፣ ባለሀብቶች በዝቅተኛ ወለድ ገንዘብ ተበድረው ከፍተኛ ትርፍ ወደሚያስገኙ ታዳጊ ገበያዎች እንዲያፈሱ ምቹ ሁኔታ ስለፈጠረላቸው ነው። የአሜሪካ መንግስት በገበያው ውስጥ ጣልቃ መግባቱ፣ የብድር ወለድ በድንገት እንዳያሻቅብ በማድረግ የባለሀብቶችን ስጋት በእጅጉ ቀንስዋል።
በቲዲ ሴኪዩሪቲስ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዓለም አቀፍ የታዳጊ ገበያ የቦንድ ፈንዶች ባለፈው ሳምንት ብቻ 967 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የገንዘብ ፍሰት አግኝተዋል፤ ይህም ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ብልጫ አለው። በሌላ በኩል ባለሀብቶች ይበልጥ አስተማማኝ ወደሆኑ የሀብት ማከማቻ አማራጮች ፊታቸውን በማዞራቸው፣ የአሜሪካው ውሳኔ ለወርቅ ዋጋ መናርም ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በለንደን የዩኒየን ባንኬር ፕራይቪ የውጭ ምንዛሬ ስትራቴጂ ኃላፊ ፒተር ኪንሴላ...የአሜሪካ መንግስት እርምጃ ዶላርን በማዳከሙ ምክንያት ከፍተኛ ወለድ የሚከፍሉ የታዳጊ ሀገራት ገንዘቦች ዋነኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለምሳሌ የቦንድ ግዢው ከተዋወቀ ወዲህ የደቡብ ኮሪያ ዎን በ2.83 በመቶ፣ የብራዚል ሪያል በ0.64 በመቶ፣ እንዲሁም የደቡብ አፍሪካ ራንድ በ0.59 በመቶ በዶላር ላይ ብልጫ ማሳየት ችለዋል።
እንደ ትንታኔው ከሆነ ብራዚል እና ቱርክ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በመሆን ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል። ብራዚል 14 በመቶ እንዲሁም ቱርክ 37 በመቶ የሆነ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ በማቅረባቸው በባለሀብቶች ዘንድ ተመራጭ ሆነዋል። በተመሳሳይ ኮሎምቢያም በዚህ ዓመት ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለች ሲሆን፣ የሀገሪቱ የገንዘብ ዋጋም ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ በ20 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በአንጻሩ እንደ ህንድ ያሉ የእስያ ሀገራት ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ያላቸው በመሆኑ (የህንድ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ምጣኔ 5.25 በመቶ ነው)፣ ከሌሎች ታዳጊ ገበያዎች አንጻር ተመራጭነታቸው ዝቅተኛ መሆኑን የስክዋክ ቦክስ እስያ ዘገባ አመልክቷል። የኢራንን ጦርነት ተከትሎ ከታዳጊ ገበያዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወጥቶ የነበረው የውጭ ገንዘብ፣ አሁን በአሜሪካ የቦንድ ግዢ ፖሊሲ ምክንያት ዳግም እያንሰራራ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አስረድተዋል።

1 month ago