“ኢትዮጵያ እንደ ግራር ትሁን!”
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)ኢትዮጵያ እንደ ግራር ትሁን ሲባል፤ ትርጉሙ ከጥልቅ ታሪካዊ መሰረቷ በመነሳት ከፍታን የሚሻ ህዝብ ያላትና የተከበረች ሀገር ትሁን ማለት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት “ ግራር በመጀመሪያ የጠለቀ ስር አለው ፤ይህም የኢትዮጵያን እሳቤ ከወቅታዊ ንፋሶች አሻግሮ የሚያስብ፣ በታሪክና በባህል የጸና ማህበራዊና ፖለቲካዊ መሰረት እንዳላት ያሳያል'' ብለዋል።
በተጨማሪም ግራር ከፍ ብሎ የሚበቅል ሲሆን፥ ይህም ትናንሽ፣ ያረጁና ኋላ ቀር እሳቤዎች ከጉዟችን እንዳያደናቅፉን አሻግሮ ማየትና ብሩህ ከፍታ ላይ መድረስ ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል።
ግራር አልፎ አልፎ ጠላት ሲያይ እሾሃማ የሆነ ቅጠል በማብቀል ራሱን እንደሚከላከል ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ሉዓላዊነቷንና ክብሯን ለማስጠበቅ የሚያስችል ጽኑ ቁመና አላት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳብራሩት፤ አስፈላጊ ሲሆን ጠላትን ማሸሸ የሚያስችል አቅም መፍጠር፣ እሾህ እያፈለቁ በጠላት አለመነካት፣ እንዲሁም ረዝሞ መብቀል ብቻ ሳይሆን ትናንሽ አካላት እንዳይቀነጥሱን ራስን መጠበቅ ወሳኝ ነው።
ይህ የመከላከል አቅም ለማንም ዛቻ ሳይሆን፣ የሀገርን ሰላም እና ነፃነት በፅናት ለማቆም የሚደረግ የሕልውና ጥንቃቄ ነው።
በሌላ በኩል ግራር በባህሪው የተቸገረን እንደሚያስጠልል ሁሉ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፍልስፍናም መርዘም ብቻ ሳይሆን በቀጣናው ያሉ እህትና ወንድሞቻችን ሲቸግራቸው ለማገዝ ዝግጁ መሆንን መሰረት ያደረገ ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ ፖሊሲም የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብሮችን የሚያጠናክር ነው፤ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ቁርኝት የጋራ ልማትን፣ ሰላምን እና የኢኮኖሚ ትስስርን የሚያቀነቅን ነው።
ሀገራችን ከጎረቤቶቿ ጋር በቅንጅት ለመሥራት፣ ለሰላም፣ ለጋራ ተጠቃሚነትና ለወንድማማችነት ሁልጊዜም በሯ ክፍት ነው።
በአንጻሩ ሉዓላዊነቷ ላይ ግን በምንም መልኩ የምትደራደር አይደለችም።
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ያላት አዎንታዊ ሚና የሚገለጸው በሃይል ሽያጭ፣ በመንገድና የትራንስፖርት ትስስር እንዲሁም በሰላም ማስከበር ሥራዎች ውስጥ በምታበረክተው የላቀ አስተዋጽኦ ነው።
የዛፉ ጥላ ለሌሎች እንደሚተርፍ ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ያላትን ሰብዓዊና የተፈጥሮ ሃብት ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ለመጋራት ያላት ቁርጠኝነት የጸና ነው።
ኢትዮጵያ በዚህ ሁለገብና ሚዛናዊ አካሄድ ጸንታ ስትቀጥል፣ ለቀጣናው ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ የሰላም፣ የልማትና የአብሮነት ምሳሌ ሆና ትቀጥላለች።
በሶስና አለማየሁ

1 month ago