የሚያመርቱ ዜጎች፣ የሚረጋገጠዉ ሉዓላዊነት፡ ኢንዱስትሪዎቻችን የፈጠሩት ተስፋ
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
አንድ ሀገር እውነተኛ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን በተግባር የምታረጋግጠው የዜጎቿን መሠረታዊ ፍላጎቶች በገዛ አቅሟ አምርታ ማቅረብ ስትችል ነው።
ለዓመታት ከቀላል የፍጆታ ዕቃዎች እስከ ከባድ ማሽነሪዎች ድረስ የውጭ ገበያን ስትማተር የኖረችው ሀገራችን ዛሬ ላይ ታሪካዊ የሆነ የመዋቅር ሽግግር በማድረግ ላይ ትገኛለች።
የመደመር መንግሥት በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ የሪፎርም እርምጃዎች ቀደም ሲል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶች አሁን በሀገር ውስጥ በስፋት መመረት መጀመራቸው የዚህ ጉዞ ማሳያ ነው።
በመደመር ዕሳቤ የተቃኘው የሀገራችን አዲሱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ ማኑፋክቸሪንግን የብልጽግናችን ዋነኛ ምሰሶ አድርጎ አስቀምጦታል።
በተለይም "ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ የተፈጠረው መነቃቃት በዘርፉ ለዓመታት ተንሰራፍተው የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት ተጨባጭ ውጤቶችን አምጥቷል። የኢንዱስትሪዎቻችን የማምረት አቅም አጠቃቀም ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በእጅጉ ከፍ ማለቱ፣ ፋብሪካዎቻችን ዳግም ሕይወት ዘርተው ሌሊት ተቀን ወደ ማምረት መግባታቸውን ያመላክታል።
ከዚህም በላይ፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በማበረታታት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተደረገው ልዩ ጥረት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ሊያወጡ የሚችሉ በርካታ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ተችሏል። ይህ የውጭ ምንዛሪን ከማዳን ባለፈ ለበርካታ ዜጎች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን የፈጠረ እና የኑሮ ደረጃን ያሻሻለ እውነተኛ የለውጥ ፍሬ ነው።
ይህንን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ፣ መንግሥት ለግሉ ዘርፍ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን በመፍጠር ረገድ መሠረታዊ የሚባሉ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ዘመናዊ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የኢኮኖሚ ዞኖች መቋቋማቸው፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ከመሳብ ባለፈ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግርን እውን እያደረጉ ነው።
በተለይም በነፃ የንግድ ቀጣናዎች ለተሰማሩ ባለሀብቶች ከታክስ ነፃ መብቶች መወሰኑ፣ መንግሥት ዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን አግኝቶ የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) የጀርባ አጥንት እንዲሆን ያለውን ቁርጠኝነት ነዉ።
በአግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳ ውጤቶች እንዲሁም እንደ ስሚንቶና ብረት ባሉ ከባድ የግንባታ ግብዓቶች ላይ እየታየ ያለው መነቃቃት የዚሁ ስትራቴጂ አካል ነው።
ሆኖም ጉዟችን በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም፤ ዛሬ የተዘራው ዘር የነገውን ግዙፍ የኢንዱስትሪዎች ማብቀሉ አይቀሬ ነው። የነበሩብንን የአቅርቦት ሰንሰለት ፈትተን በቀጣዮቹ ዓመታት ከምንጊዜውም በላይ ላቅ ወዳለ ምዕራፍ መሸጋገር ያስፈልገናል፡፡ ከቀላል የፍጆታ ዕቃዎች ባለፈ፣ ተሽከርካሪዎችን፣ ኬሚካሎችን፣ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ዉጤቶችን፣ እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎችን በሀገራችን በስፋት ማምረት ወሳኝ ይሆናል። ይህንን ለማሳካትም የሰውን ኃይል ዕውቀትና ክህሎት የሚያሳድጉ የሥልጠናና የኢንኩቤሽን ማዕከላት ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪው ትናንት የውጭ ምርቶችን ተቀባይ የነበረችውን ሀገር፣ ነገ የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ውጤቶች ላኪ ወደሆነች ሉዓላዊ ሀገርነት የመቀየር አቅም አለው።
"ኢትዮጵያ ታምርት" የሕዝባችን የዕለት ተዕለት የሥራ ባህል በመሆን የብልጽግናችን አምድ ሆኖ ይቀጥላል። እጃችንን አጣምረን የውጭውን ዓለም ከመጠበቅ፣ እጃችንን አብዝተን በማሠራት ሉዓላዊነታችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

1 month ago