የተደመረ ጉልበት፤ የነቃ ሀገራዊ አቅም
***************
(የዕለቱ መልዕክት)
የተራበን ሰው መመገብ፣ ችግር ላይ የወደቀውን ደግፎ ማንሳት የሰው ልጅ የተፈጥሮ በጎነት መገለጫ ነው። ይሁን እንጂ እውነተኛው የለውጥ እና የዕድገት ጥያቄ የሚጀምረው "ከዚያስ በኋላ?" ከሚለው መሠረታዊ ነጥብ ላይ ነው። ነገ ይኸው ሰው እንደገና የሌሎችን እጅ እንዳይጠብቅ፣ በራሱ እግር ቆሞ አምራች ዜጋ እንዲሆን ምን መሥራት አለብን? የሰው ተኮር በጎ ፈቃድና የልማት ራዕይ ትክክለኛ ምላሽ የሚሰጠው ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ ነው።
ዛሬ በሀገራችን የተጀመረው ማኅበራዊ ንቅናቄ ከወቅታዊና ከትናንሽ ግለሰባዊ ድጋፎች ወጥቶ፣ ዜጎችን ከእርዳታ ጥገኝነት ወደ ዘላቂ የሀገር ግንባታና ራስን ወደ መቻል የሚያሸጋግር ግዙፍ የለውጥ ኃይል ሆኗል።
በማኅበረሰባችን ውስጥ በደቦ፣ በእድር እና በእቁብ ሲገለጽ የኖረው የመረዳዳት እሴት ዛሬ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በዘመናዊ አሠራር ተዋቅሯል። ክረምት ለብዙዎች የዕረፍትና የቤት ውስጥ ወቅት ቢሆንም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወጣቶችና ባለሙያዎች ግን የፈረሱ ቤቶችን የሚያድሱበት፣ ደም የሚለግሱበት፣ አረንጓዴ አሻራቸውን የሚያሳርፉበትና የወደፊቱን ትውልድ የሚያንጹበት የላቀ የፍቅር ወቅት ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የክረምት ወቅት ሲደርስ፣ እኛም ለወገኖቻችን የምንዘረጋው የደግነት እጅ አብሮ ይጀግናል" በማለት እንደገለጹት ይህ እንቅስቃሴ የተደበቀውን ሀገራዊ አቅም አውጥቶ ወደ ተጨባጭ ልማት የቀየረ ታሪካዊ ክንውን ነው።
ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የተከናወኑት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ተጨባጭ ውጤቶች የዚህን አካሄድ ዘላቂነት ያረጋግጣሉ። ከ35 ሺህ በላይ የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ከ4 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የትምህርት ዕድል አግኝተዋል፤ በርካታ የገጠር መንገዶች፣ መለስተኛ ድልድዮችና የጤና ኬላዎች ተገንብተዋል።
በለውጡ ዓመታት በበጎ ፈቃድ ብቻ 157.3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የተመዘገበ ሲሆን በአዲስ አበባ ብቻ የወጣቶች አስተዋፅኦ ወደ 6.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
በ2017 ዓ.ም የክረምት ዘመቻ ከ57 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነው ከ23 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች መሳተፋቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጪን ከማዳን ባለፈ የልዩ ልዩ ማኅበረሰብ ክፍሎችን አንድነት የሚያጠናክር፣ ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥርና ሰላምን የሚያጸና መሆኑን ያሳያል።
ይህ እንቅስቃሴ ትልቁን ግብ የሚመታው ዜጎችን ከጥገኝነት አውጥቶ በራሳቸው እንዲቆሙ ሲያደርግ ነው። መንግሥት ይፋ ካደረጋቸው "የዜሮ ግቦች" መካከል ተረጂነትንና ልመናን ዜሮ ማድረግ ዋነኛው ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ ከ30 በላይ የምገባ ማዕከላት የዕለት ጉርስ ፍላጎትን ከመሙላት ባሻገር የዜጎችን ክብር ጠብቀዋል። ከዚህም በላይ በጎዳና ይኖሩ የነበሩ ወጣቶችና ሕፃናት በማገገሚያ ማዕከላት ታቅፈው የሥነ ልቦና ድጋፍና የሙያ ክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።
ሰልጣኞቹ ከ'ሌማት ትሩፋት' እና ከከተማ ግብርና ንቅናቄዎች ጋር ተቀናጅተው፣ በሥራ ፈጠራና በፋይናንስ ድጋፍ ታግዘው ራሳቸውን ወደ ቻሉ አምራች ዜጎች መቀየራቸው የተረጂነትን አዙሪት በዘላቂነት የሰበረ ስኬት ነው።
የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና በመንግሥት በጀት ብቻ ሊረጋገጥ አይችልም፤ የሚረጋገጠው ከ130 ሚሊዮን በላይ የሆነው ሕዝባችን ጉልበቱን፣ ዕውቀቱንና ሀብቱን አስተባብሮ ሲነሳ ነው።
ሰውን መርዳት በጎነት ቢሆንም፣ ሰውን ማብቃትና ራሱን እንዲችል ማድረግ ግን ዘላቂ የሀገር ግንባታ ነው። ድጋፍን ከተሳትፎ፣ ተሳትፎን ከአቅም ግንባታ፣ አቅም ግንባታን ደግሞ ራስን ከመቻል ጋር በማስተሳሰር የምናደርገው ይህ የተቀናጀ ጥረት ኢትዮጵያን ከተረጂነት አረንቋ አውጥቶ ወደ ጽኑ ብልጽግና የሚያሸጋግር የጋራ ቅርሳችን ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

1 month ago