(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የጋራ መግለጫ አወጡ፡፡ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ልኡክ ያላቸው የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ማለትም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ቡልጋሪያ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ሉክዘምበርግ፣ ማልታ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ስፔን፣ ስዊድን እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙት የካናዳ፣ የኖርዌይና የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲዎች ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመሆን ዛሬ አጠር ያለ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ጨምረውም ሁሉም አካላት የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ገንቢና ቅን በሆነ መንፈስ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ በአዲስ አበበና በመቀሌ ተገኝተው አዲስ ምክክር መጀመራቸውን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል፡፡
በከፍተኛ ድርቅና ከፍተኛ የሰብአዊነት ፍላጎት ውስጥ ባለው ትግራይ ክልል አዲስ ጦርነት መነሳቱ በህዝቡ ላይ ሌላ ቀውስ እንደሚፈጥርም መግለጫው አሳስቧል፡፡

1 month ago