Logo
FastMereja
መልካም ልደት ናርዶስ አበበ! 🎂
ዛሬ የልደቷ ቀን ነው!

የበጎነት ተምሳሌት፣ የጥንካሬ ማሳያ፣ ትህትና መለያዋ፣ የብዙ ወላጅ አልባ ህፃናት እናት፣ ሰዎችን ከስቃይ ገላግላ ጤናና ተስፋን የምትመልስ ልጅ ውቧ የአቢሲኒያ ፈርጥ!

ሞዴልና የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ናርዶስ አበበ፤ ጣሊያንን በፍቅር ያሸነፈች፣ ፍቅርን በተግባር የምታሳይ ታላቅ ሴት ናት። ዛሬም እንደ ቀደሙት ልደቶቿ ሁሉ ቀኗን ከችግረኞችና ከነዳያን ጋር በማሳለፍ፣ ምግብ በመመገብና ፍቅርን በማካፈል ላይ ትገኛለች።

አሁን ላይ የቂርቆስ መረዳጃ ዕድር አምባሳደር በመሆን የምታገለግል ሲሆን፣ ከቤዛዊት መስፍን ጋር በመሆንም ባህርዳር ላይ በእናቶችና ህፃናት ላይ በትኩረት ትሰራለች።

እውነተኛዋ የበጎነት አምባሳደራችን ናርዶስ አበበ፤ እንኳንም ተወለድሽልን! ረጅም እድሜና ጤና ይስጥሽ! ✨🎉

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.