ከ«እንታዘዝ» ወደ «እንምራ» የማያድግ የቀነጨረው የአማራ ፖለቲካ
የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዛሬው የህይወት አጋጣሚ ግለሰባዊ የታማኝነት ምስክርነት ብቻ ሳይሆን፣ የአማራ የፖለቲካ ሊሂቃን (Elites) እና የክልሉን ባለሥልጣናት ስትራቴጂካዊ ውድቀትና የራእይ አልባነት ገጽታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አሳዛኝ ክስተት ነው።
በሀገሪቱ የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ላይ ደርሰው የነበሩ መሪዎች ከስልጣን ሲወርዱ የሚጠብቃቸው ተቋማዊና ማህበራዊ ዋስትና አለመኖሩ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት እርስ በእርስ የመደጋገፍ፣ የጋራ ህልውናን የማስከበር እና የራሳቸውን ሰዎች በክብር የመጠበቅ ባህል ምን ያህል እንደወደቀ ማረጋገጫ ነው።
በየወቅቱ የስልጣን መንበር ላይ የሚወጡ የአማራ ባለሥልጣናት የራሳቸውን እና የህዝባቸውን የረጅም ጊዜ ጥቅም የሚቀርፅ ራእይ ከመሰነቅ ይልቅ፣ የማዕከላዊው አገዛዝ ታዛዥ እና የፖለቲካ መሳሪያ ሆነው ሲያገለግሉ መኖራቸው አዲስ ክስተት አይደለም።
ይህም ባለሥልጣናቱ «እንታዘዝ» እንጂ «እንምራ» የማይሉ፣ «በተቀደደልን ቦይ እንፍሰስ» እንጂ «ራሳችን ቦይ እንቅደድ» ብለው ለማስሰብ የማይደፍሩ፣ ለህዝባቸው ተሻጋሪ መንገድ ማሳየት የማይችሉ ራዕይ አልባዎች መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል።
የኦሮሚያ ክልል በአንድ ፕሬዝዳንት ይህን ያህል ጊዜ ዘላቂ አመራርና ፖለቲካዊ መረጋጋት ውስጥ ሆኖ ለቀድሞ መሪዎቹ ተገቢውን ክብርና ቤት ሰጥቶ በመንከባከብ የነባር መሪዎቹን ህይወት ዋስትና ሲያስጠብቅ፣ በአንፃሩ በዚሁ ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል የመሩ በርካታ ፕሬዝዳንቶችን (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና አቶ አረጋ ከበደን) እየቀያየረ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የመዋቅር መበታተን ሰለባ ሆኗል።
የአማራ ባለሥልጣናት የራሳቸውን እና ነባር መሪዎችን በክብር የመያዝ፣ ከስልጣን በኋላም ቢሆን እውቀታቸውንና ልምዳቸውን በመጠቀም ለህዝብ አገልግሎት እንዲያውሉ የማድረግ አቅም ማጣታቸው፣ የፖለቲካ መዋቅሩ ምን ያህል መበታተን እና መጠፋፋት እንደነገሰበት ያሳያል።
የሌሎች ክልሎችና ድርጅቶች ፖለቲከኞች ነባር አመራሮቻቸውን እንደ ትልቅ አሴት አቅፈውና ጠብቀው በሚያቆዩበት ምህዳር ውስጥ፣ የአማራ ባለሥልጣናት ግን አንዳቸው ሌላውን ከመገፋፋት፣ ከማሳደድ እና ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ እርስ በእርስ ከመበላላት አልፈው ለህዝባቸው ተሻጋሪ ራእይ ማዘጋጀት አልቻሉም።
ይህ የአቶ ገዱ የሰሞኑ ሁኔታ ለክልሉ ባለሥልጣናት ከጥልቅ እንቅልፍ የሚያባንንና «ንቁ!» የሚል ትልቅ የደወል ጥሪ ነው።
ባለሥልጣናቱ አሁንም ከዚህ የታዛዥነትና የይስሙላ ስልጣን መንፈስ ካልወጡ፣ የሚመሩትን ታላቅ ህዝብ ታሪክና የታገገለውን ዋጋ ዝቅ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ። ህዝቡን የሚመጥን መሪ ማለት በተቀደደለት ቦይ የሚፈስ ሳይሆን የራሱን ህዝብ መብትና ጥቅም የሚያስከብር መንገድ የሚቀድ፣ አርቆ አስተዋይ እና የራሱ ራእይ ያለው አመራር ነው።
ያለ ተቋማዊ አንድነት፣ ያለ እርስ በእርስ መደጋገፍ እና የራስን መሪዎች በክብር የመጠበቅ ባህልን ሳይገነቡ የሚደረግ የፖለቲካ ጉዞ መጨረሻው ውድቀትና በሌሎች መጠቀሚያ መሆን ብቻ ነው።
በመሆኑም ከነባር ስህተቶች በመማር፣ ከጊዜያዊ የታዛዥነት እና የመላላክ መንፈስ ወጥቶ የጋራ ራእይን በመቅረፅ፣ የታመኑና ሀገራቸውን ያገለገሉ መሪዎችን በክብር ማቆየት፣ የራስን ፈለግ እና ራዕይ የሚከተል ጠንካራ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅር መገንባት የቀጣይ ህልውና ወሳኝ ጉዳይ ነው።

2 months ago