Logo
Getu Temesgen
ኖቫ ኮኔክሽን እና አርትስ ቴሌቪዠን አብረው ለመስራት ተስማሙ
#ethiopia | አርትስ ቴሌቭዥን እና ኖቫ ኮኔክሽንስ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እንደዚሁም የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን በቀጣይ ሦስት ዓመታት በአብሮነት ለማዘጋጀት ስምምነት ተፈራረሙ።

አርትስ ቴሌቭዥንን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የአርትስ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ራፋቶኤል ወርቁ እንደተናገሩት አርትስ ቴሌቭዥን ኖቫ ኮኔክሽንስ የሚያዘጋጃቸው የነዚህ መርሃግብሮች አጋር የሆነው ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ዓለም ሁሉ አብሮ እየተገኘ የአፍሪካን ሕዳሴ ለማብሰር ከተነሳበት ዓላማ ጋር በእጅጉ ስለተቆራኘ ነው።

የኖቫ ኮኔክሽንስ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አብዛ በበኩላቸው ኖቫ ኮኔክሽንስ በሚያዘጋጃቸው መርሃ-ግብሮች ላይ አርትስ ቴሌቭዥን በተሻለ ዓላማው ከኛጋ የተጣጣመ አጋር ሆኖ መስራት የሚችል ተቋም በመሆኑ ነው ብለዋል።

ስምምነቱ አርትስ ቴሌቭዥን ከኖቫ ኮኔክሽንስ ጋር በመተባበር በቀጣይ ሦስት ዓመታት በአሜሪካ ዋሺንግተን ከተማ ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እና የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማካሄድ እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የስምምነቱ መፈረም መርሃግብሮቹ በአርትስ ቴሌቭዥን በኩል በሰሜን አሜሪካ ለሚገኘው የዳያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ ይበልጥ ተደራሽ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

***
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) - ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ - በኖቫ ኮኔክሽን የሚዘጋጁ ( የአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ እና የግራንድ አፍሪካን ረን ) ዝግጅቶች የኢትዮጵያ ወኪል ነው።

Getu Temesgen Media & Comminucations
is sole agent in Ethiopia for African Impact Award and Grand African Run events organized by Nova Connection.
#grandafricanrun #bettertogether #አብሮነትመሻልነው

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.