በናይጄሪያ የዲኤንኤ ምርመራ ካደረጉ አራት ወንዶች መካከል አንዱ የልጁ ባዮሎጂካዊ አባት አለመሆኑ ተረጋገጠ
#fastmereja I በናይጄሪያ በግል ተቋም የዲኤንኤ (DNA) የምርመራ አገልግሎት ከሚሰጡት ዋነኛው የሆነው "ስማርት ዲኤንኤ" ይፋ ባደረገው የ2025/2026 አዲስ ሪፖርት መሠረት፣ የአባትነት ማረጋገጫ ከተደረገላቸው ወንዶች መካከል 23.6 በመቶ የሚሆኑት የልጆቹ እውነተኛ ባዮሎጂካዊ አባት እንዳልሆኑ ተረጋገጠ። ይህም አሃዝ ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው 24 በመቶ እና በ2023 ከነበረው 26.1 በመቶ ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ቅናሽ ያሳየ ነው።
ሆኖም ዋና መሥሪያ ቤቱን በሌጎስ ያደረገው ይህ ተቋም፣ ይህ ውጤት በጠቅላላው የናይጄሪያ ሕዝብ ውስጥ ከሚገኙ አራት ሕፃናት አንዱ የሌላ አባት ልጅ ነው ማለት እንዳልሆነ በጽኑ አስጠንቅቋል። ተቋሙ እንዳብራራው ምርመራውን ለማድረግ ወደ ተቋሙ የሚመጡት ሰዎች አስቀድመው ጥርጣሬ ያደረባቸው በመሆናቸው መላውን የናይጄሪያ ሕዝብ በዘፈቀደ የሚወክሉ አይደሉም።
ከተደረጉት የዲኤንኤ ምርመራዎች መካከል አብዛኞቹ ማለትም 87 በመቶ የሚሆኑት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይም ለስደት (ኢሚግሬሽን) ጉዳይ ሳይሆን ሰዎች ለግል የአእምሮ እፎይታና ጥርጣሬን ለማጥፋት ያደረጉት እንደሆነ ተገልጻል። በተጨማሪም የዲኤንኤ ምርመራ ጥያቄዎችን ከሚያቀርቡት መካከል 79 በመቶ ያህሉ ወንዶች ሲሆኑ፣ ምርመራውን ካደረጉት ወንዶች መካከል ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጉት ዕድሜያቸው 41 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ናቸው።
የዲኤንኤ ምርመራ ፍላጎት በሌሎች የናይጄሪያ ግዛቶችም እየጨመረ የመጣ ቢሆንም፣ ከተመዘገቡት የዲኤንኤ ምርመራዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም ሶስት አራተኛው (75%) የተካሄደው የሀገሪቱ ትልቁ የንግድ ማዕከል በሆነችው ሌጎስ ከተማ ውስጥ ነው።

1 month ago