Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከ30 ዓመታት በላይ ያገለገለው ጋዜጠኛ ቅጣው ንጉሴ ከጸጥታ አካላት በደረሰበት ጫና እና ሰቆቃ ምክኒያት ሀገሩን ጥሎ መሰደዱ ታውቋል::

ጋዜጠኛ ቅጣው ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በህትመት ሚዲያ አገሬ፣ ወላፈን፣ ቤዛ፣ ዞብል በተሰኙና በሌሎችም ጋዜጦች ላይ በአዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት አገልግሏል:: ቀጥሎም በኢትዮጵያ ሬድዮ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የተለያዩ ፕሮግራሞች አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።

በሐምሌ 1997 ዓ.ም ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መልቀቂያ በማስገባት ጣቢያውን ከለቀቀ በኃላ ለረጅም ዓመታት በግሉ የማስታወቂያ ድርጅት ከፍቶ በመገናኛ ብዙሃን ስራዎች ላይ ቆይቷል።

ይሁንና በሚያቀርባቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይዘት ሳቢያ የሚደርስበትን ጫና ተቋቁሞ ቢቆይም በኢትዮጵያ ባለው የሚዲያ አፈና ምክንያት በቅርቡ ለህይወቱ አስጊ ሁኔታ በመፈጠሩ ከሀገር መሰደዱን ለጋዜጠኛው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸውልናል።

በቅርቡም የምክክር ኮሚሽኑን ሰነድ በሚስጥር ያቀበለህን ሰው ማንነት አውጣ በሚል በደህንንት አካላት ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ በመጨረሻም በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር::

በእስር ላይ እያለ በደረሰበት ሰቆቃ በመጎዳቱ ሆስፒታል ከተወሰደ በኃላ አጋጣሚውን በመጠቀም ከእስር አምልጧል::

በዚሁም የተነሳ ጋዜጠኛ ቅጣው እጅጉ ለህይወቱ በመስጋት ከአገር ጥሎ መሰደዱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.