ደራሲ አረጋይ የመጀመሪያ መጽሐፉን ከአሸንዳ በዓል ድምቀት ጋር አጣጥሞ ለንባብ አበቃ!
#fastmereja :- ደራሲ አረጋይ—በብዕር ስሙ «ቃዳዊ»—የመጀመሪያው የሆነውን «ራሔል» የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ከአሸንዳ በዓል ጋር በማያያዝ በዛሬዉ እለት በወመዘክር ቤተመጽሐፍት ኅሩይ አዳራሽ በይፋ ለአንባብያን አብቅቷል።
መጽሐፉ ደራሲው በዝግጅት ክፍል ትምህርቱ ላይ ሳለ በመምህሩ የቀረበለትን የማበረታቻ አስተያየት መነሻ በማድረግ የተጻፈ ሲሆን፣ ታሪኩም በፌስቡክ አጫጭር ጽሑፎች ተጀምሮ በአርታኢያን አቶ ግርማይ እና አቶ ብርሃኑ አባዲ ሙያዊ ድጋፍ ወደ ሙሉ መጽሐፍነት የተሸጋገረ መሆኑ ተገልጿል።
በማንኩሳ አታሚና አሳታሚ ኃላ /የተ/የግ/ማሀበር ማተሚያ ቤት በኩል የታተመዉ ይህ መፅሀፍ የታሪኩ መደምደሚያ ከአሸንዳ በዓል ጋር የተያያዘ በመሆኑ መጽሐፉ ለትግራይ ሴቶች እንደ ልዩ ስጦታ ተበርክቷል ተብሏል።
«ራሔል» የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በራሔል ገፀ-ባህሪ በኩል የሴቶችን አቅም፣ የሰላም ፍላጎት፣ ሩቅ አሳቢነት እና ፍቅር የሚያጎላ ሲሆን፤ ድምፅ የሌላቸውን ድምፅ ለማድረግ የተጻፈ ስራ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
መጽሐፉ ለብዙ አንባቢዎች ተዳራሽ እንዲሆን ታስቦ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ («ራሔል»)፣ በትግርኛ («ራሔል ጓል መቐለ») እና በእንግሊዝኛ (

2 months ago