Logo
Getu Temesgen
''ቁስላችንን አትነካኩብን'' አሜሪካ
#ethiopia ​| በታህሳስ ወር 2011 እ.ኤ.አ. ኤምቪአርዲቪ የተሰኘው የደች አርክቴክቸር ድርጅት በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ውስጥ «ዘ ክላውድ» የተሰኘ የመኖሪያ ህንፃዎች ፕሮጀክት ንድፍ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ትችትና ቁጣ አስተናግዷል።

ንድፉ 260 እና 300 ሜትር ቁመት ያላቸውን ሁለት ግዙፍ ህንፃዎች የሚያሳይ ሲሆን በ27ኛው ፎቅ አካባቢ በ10 ፎቅ ስፋት ባላቸውና አወቃቀራቸው ከተለመደው ወጣ ባሉ አራት ማዕዘን ብሎኮች እርስ በርሳቸው እንዲያያዙ ተደርገው የተሰሩ ነበሩ።

​ንድፍ አውጪዎቹ እነዚህን ተያያዥ ክፍሎች ምግብ ቤቶችን፣ የመዋኛ ገንዳዎችን፣ መዝናኛዎችንና የጋራ ቦታዎችን የያዘ «ፒክሴሌትድ ደመና» ብለው ቢጠሩትም ህንፃዎቹ ከተወሰነ አቅጣጫ ሲታዩ በግንቦቹ መካከል ያለው ብሎክ በሴፕቴምበር 11 የሽብር ጥቃት ወቅት በኒውዮርክ መንታ ህንፃዎች ዙሪያ ይታይ የነበረውን ጭስና ፍርስራሽ የሚመስል ሆኖ ተገኝቷል።

​ይህ መመሳሰል በተለይም በአሜሪካውያን ዘንድ በፅኑ የተኮነነ ሲሆን ድርጅቱ ኤምቪአርዲቪ በበኩሉ መመሳሰሉ በፍጹም ሆን ተብሎ የተደረገ አለመሆኑንና በንድፍ ሂደቱም ወቅት ያላስተዋሉት መሆኑን ገልጾ ይፋዊ ይቅርታ ጠይቋል።

ምንም እንኳን ህንፃዎቹ በ2015 እ.ኤ.አ. ተገንብተው ያልቃሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም የፕሮጀክቱ አልሚዎች በኋላ ላይ በገጠማቸው የፋይናንስ ውድቀት ምክንያት ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎቹ ሳይገነቡ ቀርተዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.