(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሱዳን እየተባባሰ የመጣው ጦርነት እና አጥፊ የጎርፍ አደጋ፣ ከ2025 መገባደጃ ወዲህ ተጨማሪ 200 ሺህ ሰዎችን ማፈናቀሉን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ። በሀገሪቱ ከሚያዝያ 2023 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ በአጠቃላይ 8.6 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በቀይ ባህር እና በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በተፈጠረው ዓለም አቀፍ የትራንስፖርት መስተጓጎል ምክንያት የረድኤት አቅርቦት ክፉኛ ተጎድቷል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ፖፕ እንደገለጹት፤ ሱዳናውያን በግጭቱ ምክንያት ውሃ፣ መብራት እና የጤና አገልግሎቶችን ከማጣታቸውም በላይ አሁን ደግሞ በከባድ የጎርፍ አደጋ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። በተለይም በሰሜን ኮርዶፋን (ኤል ኦቤይድ ከተማ) ዋናው የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት መሰረታዊ አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን፤ በብሉ ናይል፣ በምዕራብ እና ሰሜን ዳርፉር አካባቢዎችም በጦርነት እና በከባድ ዝናብ ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆነዋል። ከተፈናቀሉት ውስጥ የተወሰኑት ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውም ተገልጿል።
IOM ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ከ110 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የድንኳን እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ያቀረበ ቢሆንም፣ ይህን የዓለማችንን ትልቁን የተፈናቃዮች ቀውስ ለመታደግ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

2 months ago