3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሀበሻ አረቄ ተደፋ
በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ ተዘጋጅቶ ለዝውውር የቀረበው ይህ አረቄ በገበያ ግምቱ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ተገልጿል።
ህገ-ወጥ ምርቱ እንዲደፋ እና እንዲወገድ በተደረገበት ወቅት ግልጽነትና ህጋዊ አሰራርን በተከተለ መልኩ የሂደቱ ታዛቢዎች ተገኝተዋል።
በቦታውም የወረዳው ፖሊስ መርማሪዎች የወረዳው አቃቤ ህግ የአካባቢውም የቀበሌ ስራ አስኪያጅ የከተማዋ ነዋሪዎችና ታዛቢዎች በተገኙበት በይፋ እንዲደፋ ተደርጓል።
የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍላ ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት በማህበረሰቡ ጤና ላይ ከሚያደርሰው የጎንዮሽ ጉዳት ባለፈ በወረዳው የሚታየውን የወንጀል ድርጊት የሚያበዛና በህጋዊ የንግድ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር በመሆኑ ቁጥጥሩ አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመጠቆም እና ከጸጥታ አካላት ጋር የሚያደርገውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል ሲል ከወረዳው ኮሙኒኬሽንን ጠቅሶ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኝኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል

2 months ago