"ይህ ለእኔ የዓለም ዋንጫዬ ነበር" - ሶማሊያዊው ዳኛ ኦመር አርታን
****************
በፈረንጆቹ 2025 የአፍሪካ ኮከብ ዳኛ ክብርን የተቀናጀው ሶማሊያዊው ዳኛ ኦመር አርታን፣ ለስፖርት ህይወቱ ትልቅ ምዕራፍ የሚሆነውን የ2026 የዓለም ዋንጫ የዳኝነት ጥሪ ከፊፋ አግኝቶ ነበር።
ነገር ግን ለቅድመ ውድድር ስልጠና ወደ አሜሪካ ባደረገው ጉዞ ወቅት በትራምፕ አስተዳደር ጥብቅ የቪዛ ማጣራትና የጉዞ እገዳ መመሪያ ምክንያት ከአውሮፕላን ማረፊያ እንግልት በኋላ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ተደረገ።
በብዙ ልፋት ያመጣው የዓለም ዋንጫ ህልሙ በዚህ መልክ በድንገት ቢደናቀፍም፣ ያጋጠመው ፈተና ግን ለሌላ ታላቅ ስኬት መንገድ ከፍቶለታል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ጋር በመተባበር በፒኤስጂ እና በአስቶንቪላ መካከል የተካሄደውን የ2026 የሱፐር ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንዲመራ ለአርታን ኃላፊነቱን ሰጠው።
ይህ አጋጣሚ ኦመር አርታንን በዓለም እግር ኳስ ታሪክ የአውሮፓን የሱፐር ካፕ ፍልሚያ በመሃል ዳኝነት የመራ የመጀመሪያው አውሮፓዊ ያልሆነ ዳኛ የሚያደርገውን ታሪካዊ ስም አጎናጽፎታል።
ፒኤስጂ አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸንፎ ዋንጫውን ባነሳበት በዚህ ታሪካዊ ፍልሚያ፣ አርታን ጨዋታውን በከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና በጥራት መርቶ አጠናቋል።
ኦመር አርታን ከጨዋታው ማብቃት በኋላም በጨዋታዋ ኳስ ላይ፤ "ይህ ለእኔ የዓለም ዋንጫዬ ነበር፤ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አመሰግናለሁ፣ ህይወቴን ይበልጥ ያማረ አድርጋችሁታል" ሲል አስፍሯል፡፡

2 months ago