(ዘ-ሐበሻ ዜና) ባለፈው ወር በአንካራ፣ ቱርክ የተካሄደው የኔቶ ጉባኤ ሲጠናቀቅ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ኤር ፎርስ ዋን' ከተሰኘው ይፋዊ ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላን በአውሮፕላን ማረፊያ የምግብ አቅራቢ የጭነት መኪና በመታገዝ በድብቅ ወርደው ወደ ሌላ አውሮፕላን መቀየራቸው ተጋለጠ።
የፕሬዝዳንቱ የድብቅ ዝውውር የተካሄደው ኢራን እና አጋሮቿ ፕሬዝዳንቱ በሚሳፈሩበት አውሮፕላን ላይ የሚሳኤል ጥቃት ለማድረስ ማቀዳቸውን የሚያሳይ ተዓማኒነት ያለው መረጃ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት በመድረሱ ነው። ትራምፕ በኔቶ ጉባኤ ላይ ራሳቸውን "የኢራን ቀዳሚ ኢላማ" በማለት ጠርተው እንደነበር ይታወሳል።
ክስተቱ በዕለቱ የተፈጸመው ፕሬዝዳንቱ በካሜራ እይታ ውስጥ ሆነው ወደ አሮጌው ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን መወጣጫ ደረጃ ከወጡ በኋላ ነው። ሆኖም፣ አውሮፕላኑ ውስጥ እንደገቡ ማንም ሳያያቸው በሌላኛው በር በኩል በምግብ አቅራቢ መኪና ተደብቀው በመውረድ በአቅራቢያው ወደነበረ ሌላ የአሜሪካ መንግሥት አውሮፕላን (Air Force C-32A) ተዛውረዋል።
ሚስጥራዊው ዝውውር ምን ያህል የተሳካ እንደነበር የሚያሳየው፣ አብረዋቸው የተጓዙት ጋዜጠኞች እና የፕሬዝዳንቱ ሠራተኞች ራሳቸው ፕሬዝዳንቱ አብረዋቸው በኤር ፎርስ ዋን ውስጥ እንዳሉ አስበው መጓዛቸው ነው። ትራምፕ ዩናይትድ ኪንግደም ነዳጅ ለመሙላት ካረፉ በኋላ ካታር በስጦታ ወደሰጠችው አዲሱ የፕሬዝዳንት አውሮፕላን ተመልሰዋል። ማክሰኞ ዕለት ስለ ሁኔታው የተጠየቁት ትራምፕ፣ "ውሳኔው የጦር ኃይሉ እና የሚስጥር ጥበቃው (Secret Service) ነው፤ በእኔ ላይ ብዙ ዛቻዎች ይደርሳሉ" በማለት የተፈጠረውን አስገራሚ ክስተት አረጋግጠዋል።

2 months ago