የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና አረንጓዴ ውበት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቀናት የስራ ድካም አረፍ ለማለት፤ ከተፈጥሮ ጋር ለማውጋት የእያንዳንዱ ሰው ነፍስ የሳምንቱን ማክተሚያ ቀናት በናፍቆት ትጠብቃለች።
እነዚህ ቀናት ከአድካሚው የኑሮ እሽቅድምድም በኋላ አካልና አዕምሮን የሚያድሱበት፣ የህይወትን ትንፋሽ አድሰው የሚቀጥሉበት ወርቃማ ገፆች ናቸው።
በእነዚህ ቀናቶች የሰዎች ነፍስ አብዝታ ወደ ተፈጥሮ መጠጋትን ትሻለች፤ እረፍትና አረንጓዴነት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በተከታታይነት በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሰዎች የዕረፍት ጊዜያቸውን በሚያጣጥሙባቸው ቀናት አዲስ የህይወት ቀለም ጨምሯል።
የሰው ልጅ ከቤቱ ወጥቶ መዝናናትን ሲፈልግ በለመለሙ ስፍራዎችና በለስላሳ ነፋስ የሚወዘወዙ ዛፎች ስር አረፍ ብሎ የሰላምን አየር መማግ ቀዳሚ ምርጫው ያደርጋል፡፡
ከትርምስምሱ ገለል ብሎ በተፈጥሮ እቅፍ ውስጥ መሆን ለአእምሮ ሰላም የሚሰጠው ፈውስ ወደር የለውም።
በአረንጓዴ ዐሻራ እጆች የተደገፉና ዳግም ያገገሙ ስፍራዎች አሁን ላይ በተለይም በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የነዋሪዎች ዋነኛ የመዝናኛ ስፍራ ሆነዋል።
ለአብነትም እንደ አንድነትና እንጦጦ ፓርክ ያሉ ማራኪ የከተማ መናፈሻዎች ሰዎችን በሰፊው እቅፋቸው በመቀበል ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ የአረንጓዴነት ምልክቶች ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠብቁ ውብ መድረኮችም ናቸው።
ቤተሰቦችና ወዳጆች እጅ ለእጅ ተያይዘው ያልተበከለ አየር እየሳቡ ረጅም የእግር ጉዞዎችን ያደርጋሉ።
ንፁህ አየር እየማጉ፣ በደስታ እየተጨዋወቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከተፈጥሮ ውበት ጋር አዋህደው ያጣጥማሉ።
ይህ አይነቱ ውብ መስተጋብር በሰዎች መካከል ያለውን ፍቅር ከማጠናከሩም በላይ፤ ተፈጥሮን የመንከባከብን ጥልቅ ባህል በየቀኑ ህይወታችን ውስጥ በሂደት እንዲሰርፅ እያደረገ ይገኛል።
የዕረፍት ቀናትና የአረንጓዴ ዐሻራ ቁርኝት በመዝናናት ብቻ የሚገደብ አይደለም።
ንቁ ዜጎች፣ ወጣቶችና ቤተሰቦች የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን ወደ በጎ ተግባር በመቀየር በጥላ ስር ይሰበሰባሉ፤ እረፍታቸውን አዳዲስ ችግኞችን በመትከልና ለነገው ህይወት አሻራቸውን በማኖር ያሳልፋሉ።
ዛሬ የትናንቶቹን ዛፎች ጥላ ተጠልለን እንደምንዝናናው ሁሉ፤ እኛም በእረፍታችን የምንተክላቸው ችግኞች ለነገው ትውልድ ምቹ የመዝናኛና የህይወት ዋስትና ሆነው ያገለግላሉ።
የሰዎች የእረፍት ቀናት ምርጫና የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ፈትል በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው።
በእመቤት ሲሳይ

2 months ago