(ዘ-ሐበሻ ዜና) "የወረቀት ስምምነት የሳኡዲን ደህንነት አያረጋግጥም" ሲሉ የኢራን ባለስልጣን ተናገሩ፡፡ የኢራን የፓርላማ አባል ኢብራሂም ራዛኢ በኤክስ ገፃቸው ላይ ሳኡዲ አረቢያ ዛሬ ከቱርክና ከፓኪስታን ጋር የፈፀመችውን ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ‹‹የወረቀት ስምምነት›› በማለት የገለፁት ሲሆን ይህ ደህንነቷን እንደማያስከብር አስታውቀዋል፡፡
የኢራኑ ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ሳኡዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ስምምነትና በአሜሪካ መመካቷን አውስተው ‹‹የሪያድ መንግስት ከውጭ አገራት ደህንነት ጥበቃ ከመፈለግ ይልቅ ፖሊሲውን ቢያሻሽል ያዋጣዋል›› ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቱርክ ከሳኡዲ አረቢያና ከፓኪስታን ጋር ያደረገችው ስምምነት የመከላከል ባህርይ ያለው እንደሆነ ገልፃ ‹‹የትኛውንም አገር ኢላማ ያደረገ አይደለም›› ብላለች፡፡
የቱርክ ፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ በርሀንቲን ዱራን በኤክስ ገፃቸው ላይ ‹‹የመካ ስምምነት በማንኛውም የተወሰነ አገር ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን የ3ቱን አገራት የጋራ ደህንነትና መከላከያ የሚያጠናክር ነው፡፡ በዚህም በቀጠናችን ሰላምና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተፅኦ ያደርጋል›› ብለዋል፡፡

2 months ago