Logo
YenetaTube
የጀቱር ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመኪና ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ላይ የሚገኘው ሱዌይስ ሞተርስ ኩባንያ ወ/ሪት ልዩወርቅ ሙሃመድ (ሚስ ልዩ)ን የብራንድ የፊት ገጽ አድርጎ ሾመ።

በዛሬው ዕለት በጀቱር የመኪና ማከፋፈያ ሾውሩም በተካሄደው የጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሱዌይስ ሞተርስ ኩባንያ ወ/ሪት ልዩወርቅ ሙሃመድ (ሚስ ልዩ)ን የብራንድ ገጽአድርጎ መምረጡን የተቋሙ አመራሮችና እንግዶች በተገኙበት ይፋ አድርጓል።

ሱዌይስ ሞቶርስ ኩባንያ በአውቶሞቲቨ ኢንደስትሪ ውስጥ ቁልፍ ተሳታፊ በመሆን ባለፉት ዓመታት በነዳጅ የሚሰሩ፤ በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ (Hybrid &Plugin Hybrid) ተሽከርካሪዎችን ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂና የጥራት ደረጃ በመጠበቅ በሃገር ውስጥ በመገጣጠም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለብዙ ወገኖችን የስራ እድል በመፍጠር የሀገራችንን የአውቶሞቲቭ ኢንደስትሪን በማሳደግ የራሱን አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛል ሲሉ የኩባንያው የሽያጭ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሃመድ አብዱልቃዲር ፡፡

ሱዌይስ ሞቶርስ ለሀገር ውስጥ ገበያ ከሚያቀርባቸው የተለያዩ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያተረፉ እና በተጠቀሚዎች ዘንድም ተመራጭ የሆኑ የተሽከርካሪ ውስጥ፣ JETOUR, SUZUKI, TATA, VICTORY እንዲሁም የሶስት እግር ተሽከርካሪ ምርቶችን የሚያቀርበው BAJAJ ከብዙ በጥቂቱ ይገለጻሉ ያሉት አቶ ሙሃመድ ኩባንያው የሚገጣጥማቸውን ምርቶች ለገበያው በተመጣጣኝ ዋጋ እና በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የማከፋፈያ ማእከላትን ከፍቶ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህንኑ ተደራሽነቱን ማስፋፋት ያስችለው ዘንድ በማህበራዊ የትስስር ሚዲያዎች ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነችውን በብዝሃኑ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈችውን ው/ሪት ልዩወርቅ ሙሃመድ (Miss Leyu)ን የማስታወቂያ እና የብራንድ የፊት ገጽ አድርጎ በመምረጡ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

(Miss Leyu) ልዪወርቅ መሃማድ በበርካታ እና በተለያዪ የማስታወቂያ ዘርፎች ላይ የተሳተፈች ስትሆን፣ በማህበራዊ ድረገፅ ላይ መስታወቂየዎችን፣ በቴሌቭዝን አቅራቢነት፤ በፋሽን ዘርፍ ላይ ሞዴል በመሆን፣ እንዲሁም የግል ሀሳብዋን የኢቨንት ስራ ላይ ከዲጂታል ዶዝ ጋር በአጋርነት በመመስረት እና በማዘጋጀት፣ በኢትዮጵያ እናም በሃገር ውጭ ትልቅ ተፅዕኖ በማሳየቷ ትታወቃለች::
በዛሬው እለት የስዌስ ሞተር የብራንድ ገፅ በመሆን በድርጅቱ ያለውን ስራ፣ የጥራት ልክ እንዲሁም የማህበራዊ ሃላፊነት እሴቶቻቸውን የምትጋራ ተፅእኖ ፈጣሪ የብራንድ የፊት ገፅ በመሆንዋ የተሰማትን ድስታ ገልፃለች ።
የስዌስ ሞተር ትልቅ ሀብት በመሆን እንዲሁም ድርጅቱን በሚገባ ለማስተዋወቅ የበኩሏን ድርሻ እንደምትወጣ ገልፃለች።

(Miss Leyu) ልዪወርቅ መሃማድ ራሷ የጄቱር ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ከድርጅቱ ጋር ጠንካራ ግላዊ ግኑኝነት የላት ስሆን፣ የድርጅቱን ራዕይ በሚገባ ተረድታ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በቅርበት የቁርጠኝነት እና ለቀጣይነት ያለውን ስኬት፣ በተጨማሪም ለወደፊት ስራዎችን ለማስተዋወቅ ጥሩ ተወካይ ያደርጋታል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.