(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኬንያ ማርሳቢት ካውንቲ ሞያሌ ከተማ ውስጥ ለአንድ መኖሪያ ቤት መሠረት ሲቆፈር፣ ከጣሊያን የኢትዮጵያ ወረራ (ከ1935–1936 እ.ኤ.አ) ዘመን ጀምሮ መሬት ውስጥ ተቀብረው የቆዩ ከ4,000 በላይ ጥይቶች መገኘታቸውን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።
እንደ ፖሊስ መረጃ ጥይቶቹ የተገኙት በሞያሌ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኝ ቦታ ላይ ለአንድ ቤት መሠረት የማውጣት ሥራ ሲካሄድ ነው። መሬት ውስጥ የተቀበሩ በርካታ የብረት ቁሳቁሶችን የተመለከተው የአካባቢው ነዋሪ ጥይት መሆናቸውን በመጠራጠር ለደኅንነት አካላት ጥቆማ ሰጥቷል። የደኅንነት አባላት በቦታው ተገኝተው ባደረጉት ቁፋሮ 4,060 የሚያክሉ 8×50 ሚሊሜትር መጠን ያላቸው ጥይቶችን ማውጣት ተችሏል። ጥይቶቹ የቀደመው የጣሊያን ጦር በወቅቱ በነበረው የጦርነት ዘመቻ ወቅት ጥሏቸው የሄዳቸው እንደሆኑ የተገመተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሞያሌ ፖሊስ ጣቢያ የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ተዘዋውረው በጥንቃቄ እንዲወገዱ መደረጉ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በዚሁ ማርሳቢት ካውንቲ ቻልቢ በረሃ አቅራቢያ በሚገኘው ኮሮሌ በተባለ ቦታ አቅራቢያ የሚገኙ ጥንታዊ መቃብሮች መገኘታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። በቁጥር 50 የሚሆኑት እነዚህ መቃብሮች የተገኙት በአንድ እረኛ አማካኝነት ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የ75 ዓመቱ አረጋዊ ኤድዋርድ እንደተናገሩት፣ ቦታው በ1935 እ.ኤ.አ ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ተይዘው በብሪታንያ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ የኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች እና ስደተኞች መጠለያ የነበረ ነው።
በወቅቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን በበሽታ እና በውኃ እጥረት ምክንያት ሕይወታቸው አልፎ እዚያው ቦታ መቃበራቸውን አረጋዊው ገልጸዋል። የኬንያ ፖሊስ እና የአካባቢው አስተዳደር አካላት ቦታውን በመጠበቅ የታሪካዊነቱን መጠን እና የመቃብሮቹን ዝርዝር ሁኔታ የሚያጣራ ተጨማሪ ጥናት እያካሄዱ ይገኛሉ።
የጸጥታ አካላት በሕዝብ ደኅንነት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አለመኖሩን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ነዋሪዎች መሰል የቆዩ የጦር መሣሪያዎች ወይም ጥይቶች ሲያገኙ በራሳቸው ከመንካት ይልቅ በአስቸኳይ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡ አሳስበዋል።

3 months ago