Logo
EBC
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት
****************

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ለትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ ወሎ ሰፈር የሚኘውን የፌዴሬሽኑን ጽ/ቤት አስጎብኝተዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከአሊ አህመድ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ እና ካፍን ከመመስረት አንስቶ ውድድሩን በማስተናገድ እና ዋንጫ በማንሳት በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ስለተጫወተችው ጉልህ ሚና አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዋና ፀሐፊነት እንዲሁም በካፍ ኘሬዝዳንትነት ለረጅም ጊዜ የመሩት የአፍሪካ እግር ኳስ አባት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ካፍ አሁን ለያዘው ቅርፅ የነበራቸውን ወሳኝ ሚና አስረድተዋል።

አሊ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ዕድል ባይኖረውም ጥሩ ደጋፊ በመሆን የዳያስፖራ ኢንተግሬሽን ኘሮግራምን መዘርጋት እንዲቻል ከኢትዮጵያ ውጪ የሚጫወቱ ሌሎች ተጫዋቾችን የማነሳሳት ሚና እንዲጫወት ጠይቀዋል።

አሊ አህመድ በበኩሉ፣ በርካታ ባለተሰጥኦ ኢትዮጵያን ተጫዋቾች በውጪ ሀገራት እንደሚገኙ ገልጾ፤ በትውልደ ኢትዮጵያውያን ኢንተግሬሽን ኘሮግራም ላይ አብሮ ለመሥራት እና የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

አሊ አህመድ በኢትዮጵያ ቆይታው የደራርቱ ቱሉ ስፖርት አካዳሚን የጎበኘ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ለሊት ወደ እንግሊዝ ኖርዊች ሊገዝ መሆኑን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።

Ethiopia #eff #ebc

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.