ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ከማረጋገጥ አልፎ፣ የደህንነት ቴክኖሎጂን ወደ መላክ እየተደረገ ያለ ጉዞ
ኢትዮጵያ በጸጥታና የደህንነት ቴክኖሎጂዎች ከራሷ አልፋ የጎረቤት ሀገራትን ፍላጎት ለማሟላት እየሰራች ነው፡፡
ኢትዮጵያ የጸጥታና የደህንነት ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት በመጀመር እራሷን ከመቻል አልፋ የጎረቤት ሀገራትን ፍላጎት ለማሟላት የ2030 ራዕይ ሰንቃ በመንቀሳቀስ ላይ ናት።
ይህ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ሀገሪቱ በሳይበር ደህንነት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ላይ የጀመረችውን ትልቅ ጉዞ የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ለደህንነት እና ለጸጥታ ተቋማት የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ከውጭ ሀገራት በማስገባት ላይ ጥገኛ ነበረች።
ይሁን እንጂ አሁን ላይ ከ99 በመቶ በላይ የመከላከያ፣ የብሔራዊ መታወቂያ እና የዳታ ሲስተም የደህንነት ሶፍትዌሮች በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች እንዲበለፅጉ ተደርጓል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅርቡ በተካሄዱ የሳይበር ጥቃቶች ላይ የ99.03 በመቶ የመከላከል ስኬት በማስመዝገብ የሳይበር ደህንነት የበላይነትን በመያዝ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀዳሚ የደህንነት ተርሚናል እየሆነች መምጣቷን አሳይቷል።
ሀገሪቱ በላቁ ቴክኖሎጂዎች ትግበራ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የታጠቁ ድሮኖችን እና ዘመናዊ የጦር ጄቶችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆናለች።
ለደህንነት እና ጸጥታ ተቋማት የሚያገለግል የዲጂታል ምርመራ ላብራቶሪም ተገንብቶ ወደ ሥራ ገብቷል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የጸጥታና ደህንነትን ጨምሮ የሲቪል የቴክኖሎጂን ምርት ለማሳደግ እንደ ዋና ምሰሶ ያገለግላል።
ይህ ስትራቴጂ የብሔራዊ ደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል ግንባታ፣ ስማርት ማኑፋክቸሪንግን እና የእውቀት ሽግግር ዓላማዎችን ያካተተ ነው፡፡
በስትራቴጂው መሠረት በቀን 24 ሰዓትና በሳምንት 7 ቀናት የሚሠራ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ደህንነትን ለመጠበቅ እና የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎችን ከማምረቻው ዘርፍ ጋር ለማዋሃድም እንዲሁ ከፍተኛ ርብርብ እየደረገ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ የምህንድስና አቅምን ለማሳደግ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለመደገፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኮደሮችን የማሰልጠን እና የልዩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲዎችን የመመስረት ሥራም እንዲሁ እየተከናወነ ነው።
የኢትዮጵያ እቅድ የሀገር ውስጥ የጸጥታ ፍላጎትን ማሟላት ብቻ አይደለም። በ2030 ሀገሪቱ የምስራቅ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል በመሆን ለጎረቤት ሀገራት የሳይበር ደህንነት ሶፍትዌሮችን፣ የደህንነት መፈተሻ መሣሪያዎችን እና የዳታ ጥበቃ ሲስተሞችን ለመላክ አልማ እየሠራች ነው። ይህ ቀጣናዊ ትስስርን ከማጠናከሩ ባለፈ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ያሳድጋል።
በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር የቴክኖሎጂ የበላይነትንም ይሰጣል።
ጎረቤት ሀገራት በምዕራባውያን ወይም በሌሎች የውጭ ሀገራት የቴክኖሎጂ ጥገኝነት ላይ ያላቸውን ስጋትም ይቀንሳል።
ኢትዮጵያ የጀመረችው የጸጥታና ደህንነት ቴክኖሎጂ ምርት የሀገርን ሉዓላዊነት በራስ አቅም ከማረጋገጥ አልፎ፣ በ2030 ለአፍሪካ ሀገራት የተራቀቁ የደህንነት መፍትሄዎችን የሚያቀርብ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ላኪ ሀገር የመሆን ጉዞዋን እያፋጠነው ይገኛል።

3 months ago