የፑቲን "ስውሯ ልጅ" በፓሪስ መሸታ ቤቶች እየሰራች ነው ተባለ
#ethiopia | የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ድብቅ ልጅ እንደሆነች የሚነገርላት ኤሊዛቬታ ክሪቮኖጊክ (ሉኢዛ ሮዞቫ) ከሞስኮ የሥልጣን ማዕከል ርቃ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ውስጥ ፍጹም የተለየ ሕይወት እየመራች ይገኛል።
ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ በይፋ አባትነታቸውን አምነው ተቀብለው ባያውቁም እና ጉዳዩ በይፋ ባይረጋገጥም የተሾለኩ ሰነዶችና የምርመራ ዘገባዎች ግን የጉዞ መረጃዎቿን ዋቢ በማድረግ ደምድመዋል።
የክሬምሊን ቤተ መንግሥት ለጉዳዩ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አለመስጠቱም የታሪኩን ምስጢራዊነት ይበልጥ አጉልቶታል።
ይህች አወዛጋቢ ወጣት በፓሪስ የስነ-ጥበብ እና የባህል አስተዳደር ትምህርቷን የተከታተለች ሲሆን በምሽት ቤቶች ውስጥ ከመስራቷም በላይ በተለያዩ ስሞች በዲጄነት የሙዚቃ አጫዋችነት ሙያ ላይ ተሰማርታ ትገኛለች።
አባቷ ተብሎ የሚገመቱት ፑቲን የዓለማችንን ኃያል ሀገር ሩሲያን ከክሬምሊን ሆነው በብረት እጅ ሲመሩ እሷ ግን ማንነቷን ደብቃ በፓሪስ የምሽት ክለቦችና በስነ-ጥበብ ዓለም ውስጥ አዲስ ሕይወት መገንባቷ እጅግ አስደናቂ ንፅፅርን ፈጥሯል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

18 days ago