ኢትዮጵያ የአፍሪካን አዲስ የቱሪዝም ካርታ በጥበብ እየሳለች ነው
******************
"ኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ናት" የሚለው የቆየ አስተሳሰብ ከጊዜ ጋር በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ ይገኛል። ዛሬ ኢትዮጵያ የሺህ ዓመታት ጥንታዊ ቅርሶቿን ከዘመናዊ የቱሪዝም ልማቶች ጋር በስምምነት እያጣመረች፣ ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች አዲስና ተመራጭ የጉዞ መስመር እየሆነች ነው።
ኢትዮጵያ ታሪክን፣ ተፈጥሮን፣ ባህልን እና ዘመናዊ መሠረተ-ልማትን በአንድ ወጥ የጉዞ ተሞክሮ ውስጥ አጣምራ የምታቀርብበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።
ዛሬ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ታሪኳን ብቻ አትተርክም፤ ይልቁንም አዲስ የቱሪዝም ታሪክ በተግባር እየጻፈች ትገኛለች። ለምሳሌ ያህል፣ በቅርቡ ተገንብተው ለፍሬ የበቁት የ"ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ታላላቅ ፕሮጀክቶች፣ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት፣ ዘመናዊ መናፈሻዎች፣ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች እና አረንጓዴ ስፍራዎች ኢትዮጵያን ከባህላዊ መዳረሻነት ወደ ዘመናዊ የጉዞ ልምድ እየቀየሯት ይገኛሉ።
በጎርጎራ የጣና ሐይቅ ዳርቻ ላይ የተገነቡት ዘመናዊ የመስተንግዶ ማዕከላት፣ በወንጪ የተራራ ሐይቅን የሚያቅፉት አስደናቂ የእይታ መድረኮች፣ እንዲሁም በሀላላ ኬላ የተፈጥሮንና የታሪክን ውበት የሚያሳዩት መዝናኛዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም ገጽታ በአዲስ መልክ የሳሉት ትልልቅ ስኬቶች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም የአንድነት ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ተፈጥሮ ፓርክ፣ የሳይንስ ሙዚየም እና የአዲስ አበባ አዳዲስ አረንጓዴ መናፈሻዎች የከተማ ቱሪዝምን ወደ ላቀ የደረጃ ማማ አሸጋግረውታል።
ነገር ግን ሀገራችን የዘመናዊ ቱሪዝም ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ስታስፋፋ የትናንት ታሪኳንና ማንነቷን ከቶም አልዘነጋችም። እንደ ላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የፋሲል ግቢ፣ የሰሜንና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች፣ እሳተ-ገሞራማው የዳናኪል ምድር እና የአንትሮፖሎጂ መገኛ የሆነው የኦሞ ሸለቆ ያሉ ዓለም አቀፍ ቅርሶች ከአዳዲሶቹ መዳረሻዎች ጋር ተደምረው ለጎብኚዎች ልዩና ድንቅ የጉዞ ተሞክሮ እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ዓለም ዛሬ መዝናናትንና መጎብኘትን ብቻ ሳይሆን፣ የማይረሳ ሕያው ተሞክሮን አጥብቆ በሚሻበት በዚህ ዘመን፤ ኢትዮጵያ ያንን ፍላጎት በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በሕዝቦቿ ሞቅ ያለ ፈገግታና በዘመናዊ ልማቶቿ በአንድ ላይ አሟልታ ታቀርባለች። ዛሬ ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የምትጋብዝበት ምክንያት ትናንቷ ብቻ አይደለም፤ ብሩህ የሆነው ነገዋም ጭምር ነው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ታሪኳን በአግባቡ ጠብቃ፣ የወደፊቱን የአፍሪካ የቱሪዝም ካርታ በበላይነት እየሳለች ያለች ታላቅ ሀገር መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች።
በልዩ እሸቱ
#ebc #ethiopia #tourism #landoforigins #visitethiopia

3 months ago