Logo
Getu Temesgen
የአንጋፋው ጋዜጠኛና የኮሙኒኬሽን ባለሙያ እሸቱ ዱብ
የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተፈጽሟል
#ethiopia | በጋዜጠኝነት፣ በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን፣ በቢዝነስ ስትራቴጂ፣ በሥነ ጽሑፍና በፊልም ዘርፍ የሚታወቁት አንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቱ ዱብ በ50 ዓመታቸው አርፈዋል።

እሸቱ ዱብ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕይወት ማለፋቸው የተነገረ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በጣፎ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

ከ30 ዓመታት በላይ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ያገለገሉት እሸቱ፣ በ1987 ዓ.ም. ፋና ሬዲዮ ሲመሠረት ከመጀመሪያዎቹ ባልደረቦች አንዱ በመሆን የመዝናኛ ክፍሉን በመምራት ዘርፉ ላይ የማይረሳ አሻራ አሳርፈዋል።

ከጋዜጠኝነት ባሻገር በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን፣ ብራንዲንግ፣ ማርኬቲንግ እና የቢዝነስ ስትራቴጂ ዘርፎች በሰፊው ሠርተዋል።

በCRDA የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር፣ በዋፋ ማርኬቲንግ የብራንዲንግና መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ኃላፊ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት አማካሪና አሠልጣኝ ሆነው አገልግለዋል።

በሥነ ጽሑፍ ዘርፍም "ቀይ ልበሽ" የግጥም መድበል እና "የቅርብ ሩቅ" የተሰኘ ተውኔትን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን አበርክተዋል።

በኢኮኖሚ፣ በፖሊሲና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጽሑፎቻቸውም በስፋት ተነብበዋል።

በእውቀታቸው፣ በትህትናቸው፣ በሙያዊ ብቃታቸው እና ወጣት ጋዜጠኞችን በማብቃት በኢትዮጵያ ሚዲያ ዘርፍ ዘላቂ አሻራ አስቀምጠው አልፈዋል።

ነፍሳቸውን ይማር።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.