መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ላይ ሊሰሩ ይገባል - መኩሪያ መካሻ (ረ/ፕ)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት ይጠበቅበታል አሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን መምህር መኩሪያ መካሻ (ረ/ፕ)።
መኩሪያ መካሻ (ረ/ፕ) ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፥ ጋዜጠኞች የሀገርን ሉዓላዊነትና ክብር በሚያስጠብቁ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ በመሥራት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል።
የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን በቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን አለባቸው ያሉት መምህሩ፥ የሀገርን ጥቅም በማስከበር ረገድ በጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ገንቢ ሚናን መጫወት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ማንነትና ታሪክን ለመግለፅ ብሎም ተፅዕኖ ለመፍጠር መገናኛ ብዙሃን ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልጸው፥ ገዢ ትርክት በማስረፅና ልዕለ ኃያል ሀገር በመገንባት ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባ መክረዋል።
ይህ ወቅት ዲጂታል ሚዲያው ተጽዕኖ እያየለ የመጣበት ጊዜ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እውነተኛውን መረጃ ለይቶ መጠቀም እንዲችል መሠረታዊ ትምህርት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
ለመገናኛ ብዙሃን ውጤታማነት ፈጠራ ወሳኝ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፥ የጋዜጠኝነት ስራ ተግባርን ያስቀድማል ሲሉም አብራርተዋል።
በሠራዊት ሸሎ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ከፍል መምህር መኩሪያ መካሻ (ረ/ፕ) ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://youtube.com/watch?...

3 months ago