(ዘ-ሐበሻ ዜና) እስራኤል፣ ኢራን በቅርቡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል አዲስ እቅድ ማዘጋጀቷን የሚያሳይ የስለላ መረጃ ለአሜሪካ ማጋራቷን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሁለት ምንጮች ለሲ ኤን ኤን አረጋግጠዋል። ይህ መረጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የስልሳ ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት አደጋ ላይ በወደቀበት እና ውጥረት በነገሰበት በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል።
አሜሪካ በቅርብ ሳምንታት ኢራን ትራምፕን ለመግደል ስላላት እቅድ ተከታታይ መረጃዎችን ስታገኝ ብትቆይም፣ በዚህ ሳምንት ከእስራኤል የተገኘው መረጃ ግን ሙሉ ለሙሉ አዲስ እና የተለየ ሴራን የሚያመለክት ነው ተብሏል። ይህ የእስራኤል ሪፖርት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚወስዱትን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያጠናክሩ ተጽዕኖ ለማሳደር ታስቦ የቀረበ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ የአሜሪካ ባለስልጣናት ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የአሜሪካ መንግስት ከእስራኤል ማስጠንቀቂያ በፊት ይህንን የተለየ ሴራ ሲከታተል እንዳልነበር ምንጮቹ አክለዋል። እ.ኤ.አ በሁለት ሺህ ሀያ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ የኢራኑ ከፍተኛ ጄኔራል ቃሲም ሱሌማኒ በድሮን ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ፣ ኢራን የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ትራምፕን ዒላማ ልታደርግ እንደምትችል አሜሪካ ስታስጠነቅቅ መቆየቷ ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ ከዎል ስትሪት ጆርናል ለቀረበለት ጥያቄ ዋይት ሀውስ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት የሰጡትን መግለጫ ጠቅሷል። የአሜሪካን መሪ፣ እኔን ማጥፋት ይፈልጋሉ። በሁሉም የዒላማ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዳለሁ አይቻለሁ። እስካሁን በመጠኑም ቢሆን እድለኛ ነበርኩ፤ ግን ይሄ ብዙ ላይዘልቅ ይችላል። እነዚህ ክፉ እና በሽተኛ ሰዎች ናቸው። ይህንን ካንሰር ከስሩ መንቀል አለብን፤ ታውቃላችሁ? ካንሰርን ገና በማለዳው ቆርጦ ማውጣት ያስፈልጋል፤ አሁን እየተሰማኝ ያለውም ይሄው ነው ሲሉ ትራምፕ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ የተገደሉት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ኢራናውያን የትራምፕን ሞት ሲመኙ እና ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ትራምፕ ከኢራን ጋር እያደረጉት ባለው የዲፕሎማሲ ጥረት ላይ ጥልቅ ጥርጣሬያቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በቅርቡም ከትራምፕ ጋር በዋሽንግተን እንደሚመክሩ ይጠበቃል። ምንም እንኳን ትራምፕ ከኢራን ጋር የነበረው የመግባቢያ ሰነድ አብቅቷል ቢሉም እና በሁለቱ ወገኖች መካከል ጥቃቶች ዳግም ቢያንሰራሩም፣ ከትዕይንት ጀርባ የዲፕሎማሲ ጥረቶች አሁንም እንደቀጠሉ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ሐሙስ ዕለት አስታውቀዋል። ዋሽንግተን እና ቴህራን እስከ ነሀሴ አጋማሽ ድረስ አዲስ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ እየሰሩ ይገኛሉ።
ሀሙስ ምሽት ሊወሰዱ የታሰቡ ወታደራዊ እርምጃዎች ለዲፕሎማሲው ሲባል ቢታገዱም፣ በዩ ኤስ ኤስ አብርሀም ሊንከን የጦር መርከብ ላይ ያሉ አብራሪዎች አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ጥቃት ለመሰንዘር የሚያስችላቸውን ልምምድ በማድረግ እና የመከላከያ በረራዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። የመርከቧ አዛዥ ዳን ኪለር፣ በሺዎች ለሚቆጠሩት የመርከቧ ባልደረቦች ሁኔታዎች እየተካረሩ መምጣታቸውን አሳውቀዋል።

3 months ago