Logo
Getu Temesgen
የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተጨባጭ ማስረጃ ማግኘቱን አስታወቀ
#ethiopia | የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወይም (ICC) የሱዳኑን የእርስ በርስ ጦርነት በሚመለከት ወሳኝና ተጨባጭ መረጃ ማግኘቱን አስታውቋል።

የፍርድ ቤቱ ምክትል ዋና አቃቤ ህግ ናዝሃት ሻሚም ካን ለሮይተርስ እንደገለጹት በዳርፉር እየተፈጸሙ ባሉ የጦር ወንጀሎች እና በግጭቱ መሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ተገኝቷል ብለዋል።

ይህም በዳርፉር እየተካሄደ ባለው ምርመራ የፍትህ ሂደት ትልቅ መነሻ ወይም ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል ነው ያሉት።

አቃቤ ህግዋ እንዳሉት ማስረጃዎቹ በዳርፉር እየተፈጸሙ ያሉ ወንጀሎች ከግጭቱ መሪዎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር እንዳላቸው የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ በተለይም በ2023 በአል ጀኔና እና ባለፈው ዓመት በአል ፋሺር ከተሞች የተፈጸሙትንና የዘር ማጥፋት ወንጀል ባህሪ አላቸው የተባሉ ጥቃቶችን በዝርዝር እየመረመረ እንደሚገኝ አቃቤ ህጓ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምረመራዎቹን አጠናቆ ውጤታማ እርምጃዎችን እንደሚወስድ እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

በሱዳን እየተካሄደ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት ከሶስት ዓመታት በላይ የዘለቀ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች እንዲገደሉ እና እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ፍርድ ቤት ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #theinternationalcriminalcourt #sudanwarcrimesprobe #reutersbbcafricarsf

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.