Logo
Getu Temesgen
ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም በጎንደር የባህልና ታሪክ ጉብኝት ጀመረች
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ጥበባት አምባሳደር አድርጎ የሾማት ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ጥበብና ታሪክ ለማስተዋወቅ የታለመ ጉብኝት በጎንደር ከተማ ጀምራለች።

በቆይታዋ የጎንደር ባህል ማዕከልን፣ የሙዚቃና የቴአትር ባለሙያዎችን በመጎብኘት የባህል ጭፈራና እስክስታ ልምምድ አድርጋለች። እንዲሁም በአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት የታሪክና የኪነ ህንፃ ቅርሶችን ተመልክታ ስለ ታሪካዊ እሴታቸው ገለጻ ተደርጎላታል።

ጉብኝቱ ሩት ይርጋለም በቬትናም በሚካሄደው 73ኛው የሚስ ወርልድ ውድድር ኢትዮጵያን በምትወክልበት ወቅት የአገሪቱን ባህል፣ ታሪክና ጥበብ በብቃት ለማስተዋወቅ የሚያስችላትን እውቀት ለማጠናከር የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.