ምባፔ፣ ዴምቤሌና ኦሊሴ - አስፈሪው የፊት መስመር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋቾች አስደናቂ ጊዜ እያሳለፉ ነው፡፡
በዓለም ዋንጫ እየተወዳደሩ ከሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውዱ ስብስብ ነው፡፡
በዚህ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውድ ስብስብ ውስጥ ደግሞ ኪሊያን ምባፔ፣ ኦስማን ዴምቤሌ እና ኦሊሴን የመሳሳሉ ምርጥ ተጫዋቾች ይገኙበታል፡፡
ሁለቱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከዋክብት ኪሊያን ምባፔ እና ኦስማን ዴምቤሌ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መካከል ይገኛሉ፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በሦስት የምድብ ጨዋታዎች አራት ግቦችን አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻቶ አቀብሏል፡፡
በ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን የወሰደው ኪሊያን ምባፔ በድጋሚ የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ እየተፋለመ ነው፡፡
ኪሊያን ምባፔ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታዎች ያስቆጠራቸውን አራት ግቦች ጨምሮ በአጠቃላይ በዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ግቦች 16 አድርሷል፡፡
በዚህም ኪሊያን ምባፔ የምን ጊዜም የዓለም ዋንጫ 2ኛ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ሆኗል፡፡ በቀጣይ በሚደረጉ ጨዋታዎች ተጫዋቹ ምን ያህል ግብ ያስቆጥራል የሚለው ይጠበቃል፡፡
ሌላኛው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነው ኦስማን ዴምቤሌ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
የባሎንዶር አሸናፊው ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ በሦስት የምድብ ጨዋታዎች አራት ግብ አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻቶ አቀብሏል፡፡
ዴምቤሌ በ2026 የዓለም ዋንጫ ሐትሪክ መስራት ከቻሉ ሦስት ተጫዋች መካከል አንዱ ሲሆን÷ ፈረንሳይ ኖርዌይን 4 ለ 1 ስታሸንፍ ሐትሪክ መስራቱ ይታወሳል፡፡
ዴምቤሌ በ32 ደቂቃ ኖርዌይ ላይ የሰራው ሐትሪክ በዓለም ዋንጫ ታሪክ 2ኛው ፈጣን ሐትሪክ ሆኖም ተመዝግቦለታል፡፡የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ኤሪክ ፕሮብስት በ1954 የዓለም ዋንጫ በ24 ደቂቃ ሐትሪክ መስራቱ የሚታወስ ነው፡፡
ተጫዋቹ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ለወርቅ ጫማው በቀጣይ ጨዋታዎች የሚያደርገው ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በባየርን ሙኒክ ቤት ደምቆ ወደ ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ያቀናው ኦሊሴ የፊት መስመሩ ሌላኛው ኮከብ ነው፡፡ኦሊሴ በምድብ በተደረጉ ሦስት ጨዋታዎች ሦስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ሦስቱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋቾች በዚህ የዓለም ዋንጫ እስካሁን ድረስ በጋራ 14 ግቦች ላይ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
ይህ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ጥምረት በ2026 የዓለም ዋንጫ ለተጋጣሚዎቹ ፈታኝ ሆኗል፡፡ በቀጣይ በሚደረጉ ጨዋታዎችም የእነዚህ ሦስት ተጫዋቾች ጥምረት ተጠባቂ ነው፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

3 months ago