በኮሪደር ልማት የመደመር መንግሥትን እሳቤዎችና የሥራ ጥራት ማሳየት ተችሏል - የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ
****************
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የዘርፉን አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚገመግምበት የሴክተር ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በተከፈተው የሴክተር ጉባኤ ግምገማ፥ የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ታድመዋል።
በመድረኩ የተገኙት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፥ የኮሪደር ልማት ከተሞችን በመቅረጽና መልክ በመስጠት ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አንስተው፤ በዚህም የመደመር መንግሥትን እሳቤዎችና የሥራ ጥራት ማሳየት መቻሉን ገልጸዋል።
በሀገራችን እየተከናወነ ያለው የመንገድና የኮሪደር ልማት፣ በበለጠ ትስስር የበለጸገች ፍትሐዊት ሀገር የመመስረት ራዕይን የሚያሳካ ስለመሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።
በከተሞች የታየውን አስደማሚ ስኬት በገጠር ኮሪደር ልማት በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሠራም በጉባኤው ተመላክቷል።
የመደመር መንግሥት ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ የተጀመሩትን በጥራት በማጠናቀቅ ረገድ በትኩረት እየሠራ ስለመሆኑም ተነስቷል።
በጥቅሉ ዛሬ በየቦታው እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትን ታታሪነትና ትጋት ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ናቸው ተብሏል።
የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሕዝብ፣ የመንግሥትና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው የተባለ ሲሆን፣ በቀጣይም የመሠረተ ልማት ውጥኖችን በትብብር በመፈጸም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት መረባረብ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።
#ethiopia #urbandevelopment #urbancorridor #ebc

3 months ago