በ2026 የዓለም ዋንጫ ውዱ ስብስብ - የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ 48 ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከሚሳተፉ 48 ሀገራት መካከል ውዱ ስብስብ በመሆን በቀዳሚነት መቀመጥ ችሏል፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ 1 ነጥብ 52 ቢሊየን ዩሮ እንደሚያወጣ የትራንስፈር ማርኬት ዘገባ ያመላክታል፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ኪሊያን ምባፔ፣ የባሎንዶር አሸናፊው ኦስማን ዴምቤሌ፣ ኦሊሴ፣ ሪያን ሼርኪ፣ ዴዝሪ ዱዌ እና ዊሊያም ሳሊባን የመሳሰሉ ከዋክብቶች ይገኛሉ፡፡
በ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ የሚመራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ለ2026 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ቅድመ ግምት ከተሰጣቸው ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አንዱ ነው፡፡
በጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ እየተሳተፉ ከሚገኙ ሀገራት መካከል 2ኛው ውድ ስብስብ ሆኗል፡፡
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስበስብ 1 ነጥብ 36 ቢሊየን ዩሮ እንደሚያወጣ ግምት ተሰጥቷል፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ ሃሪ ኬን፣ ዴክላን ራይስ፣ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ሬስ ጀምስ፣ ቡካዮ ሳካ፣ ኒኮ ኦሬሊ፣ ሞርጋን ሮጀርስ፣ ኤዜ፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ጎርደንን ጨምሮ በርካታ ከዋክብቶች ይገኛሉ፡፡
ይህ በ2026 የዓለም ዋንጫ 2ኛው ውድ ስብስብ እንግሊዝን ከ1966 በኋላ በድጋሚ በመድረኩ ሻምፒዮን ያደርግ ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር ለሻምፒዮንነት ቅድመ ግምት ካገኙ ሀገራት መካከል አንዱ የሆነው የስፔን ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 3ኛው ወድ ስብስብ ሆኗል፡፡
በአሰልጣኝ ሊዊስ ዴላፎንቴ የሚመራው የስፔን ብሔራዊ ቡድን 1 ነጥብ 22 ቢሊየን ዩሮ እንደሚያወጣ ተገምቷል፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ ላሚን ያማል፣ ፔድሪ፣ ጋቪ፣ ሮድሪ፣ ዴቪድ ራያ፣ ፋቢያን ሩሂዝ እና ፌራን ቶሬስ የመሳሰሉ ከዋክብት ይገኙበታል፡፡
በስፔናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የሚመራው የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በ1 ቢሊየን ዩሮ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ 4ኛው ውድ ስብስብ መሆን ችሏል፡፡
የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በስብስቡ ውስጥ የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ብሩኖ ፈረንናዴዝ፣ ቪቲኒሃ፣ ኔቬስ፣ በርናርዶ ሲልቫ እና ኑኖ ሜንዴዝን ጨምሮ በርካታ ከዋክበቶችን ይዟል፡፡
በአሰልጣኝ ዩሊያን ኔግሌስማን የሚመራው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በ947 ሚሊየን ዩሮ 5ኛው ውዱ ስብስብ ሆኗል፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አንጋፋው ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኑየር፣ ፍሎሪያን ቨርትዝ፣ ካይ ሀቨርትዝ፣ ጀማል ሙሲያላ እና ጆሹዋ ኪሚችን ጨምሮ የተለያዩ ኮከቦች ይገኙበታል፡፡
ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ እና ቤልጂዬም እንደ ቅደም ተከተላቸው ከ6ኛ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

4 months ago