እንኳን ወደ የ10000 ሀይቅ ባለቤቷና ወደ የምንኮራባት ቤታችን ሚኒሶታ በሰላም መጡ ።
በዶ/ር ሲራክ ሀይሉ።
የሚኒሶታ ትውልደ ኢትዮጵያን ሆይ፤ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) ለመታደም ወደ ሚኒሶታ የሚመጡ እንግዶችን እንቀበል።
ይህ አመት ለኛ ኮሙኒቲ እጅግ በጣም የተለየ ነው። ምክንያቱም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእስፖርት ፌዴሬሽን(ESFNA) የሚያዘጋጀው አመታዊ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሚኒሶታ መንታ ከተሞቻችን ሚኒያፖሊስ እና ቅዱስ ጳውሎስ (ሴንት ፖል) ከተሞች ይመጣል።
ESFNA እንደሚታወቀው በሰሜን አሜሪካ ብዙ ዲያስፖራ ለስፖርት እና ለባህል አከባበር የሚሰበሰብበት ዝግጅት ነው። በርከት ያሉ ከመላው ዩናይትድ ስቴትስ እና ከዚያ ውጪም የሚመጡ ጓደኞቻችን ፣ ዘመዶቻችን እንዲሁም ሌሎች ጎብኚዎች ወደዚህ ይተማሉ። ይህም እንደ ሚኒሶታ ኮሙኒቲ አባልነታችን እንግዶቹን ሞቅ ባለ ሁኔታ፣ በኩሩና ጨዋ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ የመቀበል እድል እንዲኖረን ያደርጋል።
እንደሚታወቀው ሚኒሶታ ለብዙዎቻችን ቤታችን ናት። በተለይ ለኔ እንደ አንድ ግለሰብ ላለፉት 30 አመታት መልካም ቤቴ ሆና ቆይታለች። በትጋት የምንሰራባት፣ ቤተሰብ የምናፈራባት፣ ቢዝነስ የምንገነባበት እና እርስ በርስ የምንደጋገፍበት ከተማችን ነች። ባለፉት አመታት ውስጥ የሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ጠንካራና ንቁ ሆኖ ለማገል ባሉው ሁሉ አቅም ሳይሰለች እየለፍ እንደሆነ አግኝቸዋለሁ።
ማየት ያለብን ከESFNA ዝግጅት ወደዚህ መምጣት የምናገኘዉ የእስፓርት ዝግጅቱን የመሳተፍ እና የማህበረሰባችንን በአንድ ላይ ተሰብስቦ የማየትን ዕድል ብቻ ሳይሆን የመንታ ከተሞቻችንን ውበት፣ ባሕልና ደማቅ መንፈስ ለእንግዶቻችን የምናሳይበት ነው። ሚኒሶታ የባለ10000 ሐይቆች ስቴት ናት። በእርግጥ የስቴቷ ሀይቆች ብዛት ከ11000 በላይ ነው ይባላል። ለዚህ ነው ተፈጥሮ፣ ውሃ እንዲሁም የተዋበ ከባቢ በሚኒሶታዊያን ዘንድ ወሳኝ የህይወት አካል የሚሆኑት ።
እንግዲህ የምትቀበሏቸው ጓደኞች፣ ዘመዶች ወይም የኮሚኒቲ አባለት ካሉ ዞር ዞር አርጋችሁ ብታሣዩአቸው መልካም ይሆናል። መንታ ከተሞቻችን ሊጎበኙ የሚገቡ ብዙ ውብ ቦታዎች አሉዋቸው። ከሁሉም እጅጉን ተመራጭ የሚሆነው የጉብኝት ስፍራ የሚንሀሀ ገራሚ ፏፏቴ እና ፖርክ ሲሆን ለጉዞ፣ ሰውነት ለማፍታታት እና ቆንጆ ቆንጆ ፎቶግራፎችን ለመነሳት ይመቻል ። በተጨማሪም ጎብኚዎች ታሪካዊውን የስቶን አርክ ድልድይ አቋርጦ መሄድ ሊያስደስታቸው ይችላል። ምክንያቱም ይህ ጉዞ የሚሲሲፒን ወንዝ ማራኪ ገፅታ እና የሚኒያፖሊስን እስካይላይን ለማየት ስለሚያስችላቸው ነው። አካባቢንና ጥበብን ለሚያደንቁት ደግሞ የሚኒያፖሊስ የቅርፃቅርፅ ጋርደን መታየት የሚገባው ስፍራ ነው። ይህ ቦታ ዝነኛዉ ስፑንብሪጅ ኤንድ ቼሪ የሚገኝበት ሲሆን በእግር እየተጋዙ ለመጎብኘት በጣም ተመራጭ ስፍራ ነዉ፡፡
ሸመታና መዝናናትን ለሚሹ ደግሞ በአሜሪካ ትልቁ የገበያ አዳራሽ የሆነዉን ሞል ኦፍ አሜሪካን ብናሳያቸዉ በጣም ይደሰታሉ፡፡ ሞል ኦፍ አሜሪካን በሬስቶራንቶች ፣ በመደብሮች እንዲሁም በቤት ዉስጥ የመዝናነኛ ፓርኮች የታደለ ስፍራ ነዉ፡፡ በእግር በቢስኪሊት የሚኒሶታን የተፈጥሮ ዉበት ለማድነቅ ደግሞ ቅጥልጥል ሀይቆቿ በተለይም በደ ማካ ሳካ እና ሀሪየት ሃይቅን ማይት መንፈስን ያድሳል፡፡
በእርግጥ እናዉራ ካልን ከእንግዶቻችን ጋር የሚኒሶታ ቆይታን የማይረሳ ለማድረግ ከቤት ዉጭ ያሉ አማራጮች ይመከራሉ፡፡ በእግር እንጓዝ ቢባል፣ በቢስክሊት ብንል ወይ ደሞ በአካባባዉ ያሉ ትናንሽ ጅልባዎችን ተከራይትን ለመናፈስ ብናስብ የመንታ ከተሞቹን የሚመስጥ ዉበት እናደንቅበታለን፡፡
የእንግዶችዎ ምርጫ ደግሞ ቅዱስ ጳዉሎስ ከሆነ ወደ ሚያምረዉና ከቤተሰብ ጋር ሆኖ ለመዝናናት ወደ ሚመቸዉ ወደ ኮሞ ፓርክ አና የእንስሳት መጠበቂያ ወይንም ታሪካዊዉንና በሃገሪቱ ካሉ ቤተ እምነቶች ሁሉ በጣም ተደናቂ የሆነዉን የቅዱስ ጳዉሎስ ካቴድራል ልናስጎበኛቸዉ እንችላለን፡፡ እዛዉ አቅራቢያ የሚገኘዉም የሚኒሶታ ስቴት ካፒቶልም የሚኒሶታን ታሪክና ቅርጻ ቅርጽ ለመመልከት ያስችላል፡፡
ታሪክና ባህልን የሚያደንቁ ጎብኚዎች ካጋጠሞትም አይጨነቁ በሚሲሲፒ ወንዝ ዳርቻ ላይ ወደሚገኘዉ የሚል ሲቲ ሙዚየም አሊያም በአለም ትልቅ ደረጃ ያለዉ የሚኒያፖሊስ ኢኒስቲትዩት ኦፍ አርትን ታስጎበኙዋቸዋላችሁ፡፡
ለኮሚኒቲያችን ሌላ ጠቃሚ ሃሳብ የሚሆነዉ ደግሞ እንግዶችን ስንቀበልም ሆነ ስናስተናግድ በተቀናጀ መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በሚኒሶታ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በየአካባቢዉ በቡድን በቡድን ተደራጅተን ብንሰራ ዉጤታማ የምንሆን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ አንዳችን የሌሎቻችንን እንግዶቻች ወደ የጋራ ዝግጅቶች ፒክኒክ ባርቢክዩ ወደ ሃይቅ ዳር ጉዞ እና ወደ ጥቃቅን ስብስቦች መጋበዝ እንችላለን፡፡ ከተለያየ አካባቢ የመጡ እንግዶች አንድ ላይ ሲገኛኙ ትዉስታዉ ህይወት ያለዉ እና የላቀ ይሆናል፡፡ ይህም ሰዎች ቀጣይ የሆነ ወዳጅነት እንዲያጎለብቱ እና የኛን የሚኒሶታ ኮሚኒቲ የአንድነት ስሜት ይበልጥ እንዲረዱት ያደርጋል፡፡
ESFNA ከስፖርት ዝግጅትነት ያለፈ ነዉ ኮሚኒቲን ባህልን እና አንድነትን የምናከብርበት ነዉ፡፡ እስቲ እንግዶቻችንን በኩራትና በደግነት እንቀበላቸዉ፤ ዉብ ከተሞቻችንን እናሳያቸዉ ከድንቁ ማህበረሰባችን ጋር እናስተዋዉቃቸዉ እና የሚኒሶታ ቆይታቸዉን የማይረሳ እናድርግላቸዉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኒያላ ስፓርት ክለብ የኢትዬጵያ መሀበር በሚኔሶታ ባጠቃላይ ሚናሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሊመሰገኑ ይገግባል፣፣
መልካም ቆይታ።
ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ከሚኔሶታ
የካሪዮፕራክቲክ ሐኪም

4 days ago