Logo
Getu Temesgen
የኩዌት መንግስት የቤት ውስጥ ሰራተኞችን መቅጠር የሚቻልባቸውን ሀገራት ቁጥር ወደ 10 ብቻ ገደበ
#ethiopia | የኩዌት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የቤት ውስጥ ሰራተኞች ቅጥርን የሚቆጣጠር አዲስ መመሪያ ማውጣቱን የገልፍ ኒውስ ዘገባ አመላክቷል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው አዲስ የስራ መመሪያ መሰረት፣ ከዚህ ቀደም ይፈቀድላቸው ከነበሩት ሀገራት መካከል በ27ቱ ላይ እገዳ የጣለ ሲሆን፣ ፍቃድ የተሰጣቸው ሀገራትን ቁጥር ደግሞ ወደ 10 ዝቅ አድርጓል።

አዲሱ መመሪያ የቤት ውስጥ ሰራተኞችን ማስገባት ይቻላል ብሎ ከፈቀደላቸው 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚገኙበት ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ፣ ቤኒን፣ ፊሊፒንስ፣ ስሪላንካ፣ ህንድ፣ ቪየትናም፣ ኔፓልና ሴኔጋል የተፈቀደላቸው ቀሪዎቹ ሀገራት ናቸው።

ሙሉ በሙሉና በከፊል እገዳ ከተጣለባቸው 27 ሀገራት መካከል እንደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ናይጄሪያ፣ ጅቡቲ፣ ካሜሩንና ማዳጋስካር የመሳሰሉ የአፍሪካና የእስያ ሀገራት ይገኙበታል። ለአንዳንድ ሀገራት የተጣለው እገዳ ሴት ሰራተኞችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፣ ወንዶችን መቅጠር ግን እንደሚቻል ተጠቅሷል።

ሆኖም ይህ አዲስ መመሪያ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴርና የሰው ኃይል ባለስልጣን በጋራ ባቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ መሰረት የቤት ውስጥ ሰራተኞች ዘርፍ ላይ ያለውን ቁጥጥር ይበልጥ ለማጥበቅ የወጣ መሆኑ ተገልጿል ያለው ቻነል ዋን ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.