Logo
EBC
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል
*****************

6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 02 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ያካሂዳል።

ም/ቤቱ 24ኛ መደበኛ ስብሰባው የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና ውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን የሚያፀድቅ ይሆናል።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ምክርቤት

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.