(ዘ-ሐበሻ ዜና) የመናዊያን በዝቅተኛ ደመወዝ በሚቀጠሩ ኢትዮጵያዊያን መማረራቸውን ገለፁ፡፡ እድሜው በ30ዎቹ ውስጥ የሚገኘው ዛሂድ አል ዛቢዲ አምስት ቤተሰቦቹን ለመርዳት ያገኘውን ሲሰራ መቆየቱን ይናገራል፡፡ ለሚድል ኢስት ሞኒተር ሲናገር ‹‹ለ15 አመታት ያህል በሬስቶራንቶች ሰሀን በማጠብና ቤት በማፅዳት ስራ ተሰማርቼ ቆይቻለሁ፡፡ የምችለው ስራም ይህ ብቻ ነው›› ብሏል፡፡ ጨምሮም ‹‹በፊት በቀላሉ ስራ አገኝ ነበር፡፡ አሁን ግን ስራ ማግኘት ከባድ ሆኗል›› ያል ዛቢዲ የዛሬ 7 አመት የተሻለ ገቢ ለማግኘት ወደአደን መሄዱን ገልጿል፡፡ በሚሰራው የቀን ስራ ኑሮውን እየደገፈ መቆየቱን ጠቅሷል፡፡ ሲቀጥልም ‹‹እኔ በአደን በርካታ ሬስቶራንቶች ውስጥ ስሰራ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ከቀን ወደቀን ሁኔታው እየባሰበት ሄዷል፡፡
ምክንያቱም ሬስቶራንቶች የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችን ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በማንኛውም ክፍያ ለመስራት ፈቃደኛ በመሆናቸው ሬስቶራንቶቹ የሚመርጡት እነሱን ነው›› ብሏል፡፡ አል ዛቢዲ እንደሚለው በፊት ይከፈለው የነበረው 130,00 የየመን ሪያል ወይንም 83 ዶላር ገደማ ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊያን ግን እሱ የሚሰራውን ስራ በ80,000 ሪያል ወይንም በ51 ዶላር ተቀብለው እንደሚሰሩ አስረድቷል፡፡
ለኢትዮጵያዊያኑ የሚከፈለውን ደመወዝ ተቀብሎ ቤተሰቡን ማስተዳደር እንደማይችልም አስታውቋል፡፡ ሲናገርም ‹‹ኢትዮጵያዊያን እዚህ ምንም ቤተሰብ የላቸውም፡፡ በማንኛውም ገንዘብ ተቀጥረው ቢሰሩ ህይወታቸውን መምራት ያስችላቸዋል፡፡ እኔ ቤተሰቤን የማስተዳድርበትን ስራ እነሱ እየወሰዱብኝ ነው›› ሲልም አስረድቷል፡፡ ለጋዜጣው አስተያየት የሰጡና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ኢትዮጵያዊያን በዝቅተኛ ደመወዝ የሚቀጠሩት በየመን የመቆየት እቅድ ስለሌላቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ዋነኛ አላማቸው ሳኡዲ አረቢያ መግባት መሆኑን የጠቀሱት ስደተኞቹ ስራ የሚሰሩት የቀን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ብቻ መሆኑን መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡

3 hours ago