Logo
Getu Temesgen
በመገናኛ ዲያስፓራ አደባባይ ተከስቶ በነበረው የትራፊክ አደጋ ምክንያት ተዘግቶ የቆየው መንገድ በድጋሚ ተከፈተ
#ethiopia | በመገናኛ ዲያስፓራ አደባባይ የታክሲ መቆሚያ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የመንገድ ትራፊክ እንቅስቃሴ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ መመለሱ ታውቋል።

አደጋው የተከሰተው ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ገደማ ሲሆን፣ ቅጥቅጥ ተብሎ የሚጠራው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ኋላ በሚያሽከረክርበት ወቅት ከላይኛው ተርሚናል ወደ ታችኛው ተርሚናል ወድቆ ተንጠልጥሎ በመገኘቱ መንገዱ እንዲዘጋ ሆኖ ነበር።

በዚህ አደጋ ሳቢያ በሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ተጎጂዎቹም በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የየካ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጋሻሁነኝ ሙሉጌታ ለሚዲያ እንደተናገሩት፣ የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ባለሙያዎች ተሽከርካሪውን ከቦታው ለማንሳትና ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በወቅቱም ከቀበና ተነስተው ወደ ኮተቤ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን በኩል ያለውን አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንገዱ ሙሉ በሙሉ ክፍት ተደርጎ የትራፊክ ፖሊሶች እንቅስቃሴውን እያሳለጡት ይገኛል።
#የአዲስአበባፖሊስ #የትራፊክአደጋ #መገናኛ #የየካክፍለከተማ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.