Logo
SeledaPost
ጅቡቲ በዳመርጆግ የነዳጅ ማከማቻ ግንባታ ላይ የኢትዮጵያን ድጋፍና ተሳትፎ እየጠበቀች መሆኑን ገለጸች

የጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ ቀጠናዎች ባለስልጣን በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ በኩል በሚገኘው አዲሱ የዳመርጆግ ፈሳሽ ጭነት ወደብ ላይ የነዳጅ ማከማቻ ዴፖ ግንባታ ለመጀመር በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያን ተሳትፎና የገንዘብ ድጋፍ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ሰብሳቢ አቡበከር ኦማር ሀዲ ለካፒታል እንደገለፁት ፣ ዘመናዊው የነዳጅ ወደብ ወደ ስራ እንዲገባ  የነዳጅ ማራገፊያ ዴፖ ግንባታ ይቀረዋል።

ለዚህም ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር ድርድር እያደረገ ሲሆን፣ ተቋሙ ሐምሌ 1 ቀን በሚጀምረው አዲስ የበጀት አመት በጀት አፀድቆ ለስራው እንደሚመጣ ይጠበቃል ሲሉ ነው የገለፁት።

Seledadotio
Seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.