(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲስ አበባ የተጠራው የሱዳን ፖለቲካ ሀይሎች ስብሰባ ውዝግብ ፈጠረ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ አንስቶ ለሚቀጥሉት ቀናት የሚካሄደው የሱዳን ፖለቲካ ሀይሎች ውይይት ከጅምሩ ውዝግብ ተፈጥሮበታል፡፡ ስብሰባው የተጠራው አምስትዮሽ ሀይሎች ማለትም በአፍሪካ ህብረት፣ በኢጋድ፣ በተመድ፣ በአውሮፓ ህብረትና በአረብ ሊግ አማካኝነት ነው፡፡
የስብሰባው ዋነኛ አላማም ባለፈው ወር በበርሊን በተከናወነው 3ተኛው የሱዳን አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ያልተሳተፉ የፖለቲካ ሀይሎችን አገናኝቶ እንዲወያዩ ማድረግ ነው፡፡ በስብሰባው ላይ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ አስቀድመው ገልፀው የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ሰአት ግን ራሳቸውን ማግለላቸውን የገለፁ ፓርቲዎች እንዳሉ ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ በተለይም ‹‹ሶሙድ›› በሚል የሚጠራው የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈው ግንባር ክፍፍል መፍጠሩን አስረድቷል፡፡
በቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የሚመራው ሶሙድ ውስጥ ከተጠቃለሉት ፓርቲዎች መካከል የተወሰኑት አዲስ አበባ ሲገቡ የተወሰኑት ደግሞ መቅረታቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የመሀመድ ዳጋሎ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል አጋር የሆኑ ፓርቲዎች እየተሳተፉ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው በሌተና ጄኔራል አልብሩሀን የሚመራው መንግስት ጥሪ ቢደርሰውም ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ገልጿል፡፡ አምስቱ ቀጣናዊና አለም አቀፍ ድርጅቶች ያዘጋጁት ይህ ስብሰባ በሁለት የተከፈለ ሲሆን ዛሬ የተጀመረው አንደኛው ክፍል ነው፡፡ በቀጣይነት ማለትም ከጁላይ 8 እስከ 9 ሌላ የሱዳን ፖለቲካ ሀይሎችን ያሳተፈ ስብሰባ እንደሚደረግም ዘገባው አስታውቋል፡፡

12 hours ago