ደሴ‼️
በደሴ ከተማ የአይጥ መርዝ ለበርካታ ሰዎች ህልፈት ምክኒያት ሆኗል ተባለ።
በ2018 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት የኬሚካል መመረዝ ጉዳት ለደረሰባቸው በርካታ ሰዎች ህክምና መስጠቱን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።የሆስፒታሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ብርሃኑ አዱኛ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ሆስፒታሉ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የኬሚካል መመረዝ አደጋ ለደረሰባቸው 1መቶ 72 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።
ከእነዚህ መካከል 6.8 በመቶ የሞት ምጣኔ መመዝገቡን ገልፀው በሆስፒታሉ በተሰራው የተቀናጀ ስራ ከመመረዝ ጋር የተያያዘ የሞት ምጣኔ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 27.3 በመቶ ቀንሷል ብለዋል።የጉዳቱን የስርጭት መጠን አስመልክቶ 67 በመቶ የሚሆነው ከደሴ እንዲሁም 29 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከደቡብ ወሎ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል።
እነዚህ አካባቢዎች በኬሚካል መመረዝ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ የማህበረሰብ ክፍሎች መገኛ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ብርሀኑ በሆስፒታሉ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።86.5 በመቶ የሚሆኑት ራሳቸውን ለማጥፋት በሚል ህብረተሰቡ አይጥን ለመግደል የሚጠቀምባቸውን መርዞች የተጠቀሙ ናቸው።
የመርዝ ዓይነቶች ትንታኔ እንደሚያሳየው የአይጥ መመረዝ 35.9 በመቶ ፣ የመድኃኒት መመረዝ 17.6 በመቶ እንዲሁም የበረኪና መመረዝ ደግሞ 15.3 በመቶ ድርሻን ይይዛሉ።
Seledadotio

2 days ago