Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ትውልደ ሶማሊያዊቷ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ኢልሀን ኦማር፣ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ምርጫ አስመልክቶ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት.. የኢትዮጵያ መንግሥት የሕዝቡን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫን ማረጋገጥ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ኮንግረስ አባሏ በመልዕክታቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የመምረጥ መብት እንደሚገባው ጠቅሰው ዓመታት ግጭት እና ስቃይ በኋላ፣ ሕዝቡ ሰላም፣ ፍትሕ እና ሉዓላዊ ድምፁ ሊከበርለት ይገባል" በማለት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።

ይሁን እንጂ ይህንን የኮንግረስ አባሏን የክስ መልዕክት ተከትሎ፣ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ አምባሳደር ቲቦር ናጅ ፈጣን እና ጠንከር ያለ አጸፋዊ ምላሽ ሰጥተዋል። አምባሳደር ቲቦር ናጅ በሰጡት ምላሽ፣ የሶማሊያ ሕዝብም ይህንኑ ተመሳሳይ መብት እንደሚገባው በማስታወስ ኮንግረስ አባሏን ክፉኛ ተችተዋል።

አምባሳደር ቲቦር ናጅ በመልዕክታቸው "የሶማሊያ ሕዝብም ይሄው ይገባዋል። በሞቃዲሾ ካሉት ሙሰኛ፣ ብልሹ እና አቅመ ቢስ የፖለቲካ ልሂቃን አንጻር ለምን ለሶማሊያ ሕዝብ መብት አትከራከሪም?" በማለት ኢልሀን ኦማር በትውልድ ሀገራቸው ሶማሊያ ባለው የፖለቲካ ቀውስ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ላይ ለምን ድምፃቸውን እንደማያሰሙ ጠንካራ ሞጋች ጥያቄ ሰንዝረዋል።

ይህ የሁለቱ ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎች የቃላት ልውውጥ፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ዙሪያ የሚሰጡ አስተያየቶች እንዴት ከቀጠናዊ የፖለቲካ ፍላጎቶች እና የሌሎች ሀገራት ጉዳዮች ጋር እንደሚነጻጸሩ ትኩረት የሳበ ክስተት ሆኗል።

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.