Logo
EBC
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ድምጽ ሰጡ
************************

እየተካሄደ ባለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል ቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ፋና ቁጥር 2 የምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ተወዳዳሪዋ “ዲሞክራሲያዊ የመምረጥ መብቴን፣ የዜግነት መብቴን ተጠቅሜ መርጫለሁ” ብለዋል።

አክለውም ሕብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ ለመምረጥ እያደረገ ያለው ተሳትፎ እጅግ የሚያኮራ እና ሕዝቡ ስለ ዜግነቱ እንዲሁም ስለ ሀገሩ የሚያስብ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

መሀመድ ፊጣሞ
#ebcdotstream #ethiopiaisvoting #ethiopia

4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.