Logo
FBC
የምርጫ ሂደቱ በጥሩ መንገድ እየተከናወነ ነው - ኡሁሩ ኬንያታ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት በጥሩ መንገድ እየተከናወነ ነው አሉ የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች መሪ ኡሁሩ ኬንያታ፡፡

ኡሁሩ ኬንያታ አጠቃላይ የምርጫ ሂዲቱን ተዘዋውረው መመልከታቸውን በመጥቀስ በጥሩ መንገድ እተከናነወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

ምርጫ ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም መሪያቸውን የሚመርጡበት መሆኑን ገልጸው÷ እንደ አሕጉር ይህ እንዲሳካ የአፍሪካ ሕበረት አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ የአሕጉሪቱ መቀመጫ እንደመሆኗ እዚህ የተሳካ ምርጫ መደረጉ ለመላው የአፍሪካ ሀገራት ታላቅ ተምሳሌት ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያንም መብታቸውን በመጠቀም እንዲመርጡ በማሳሰብ ምርጫው በጥሩ ሁኔታ እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

በአቤል ነዋይ

5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.