በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በ46 ምርጫ ክልሎች ምርጫ አይደረግም
ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ሥራዎች እና የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህም በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በአጠቃላይ በ46 ምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደማይደርግ አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ፣ በአማራ ክልል በ8፣ በትግራይ ክልል ደግሞ በ38 የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደማይካሄድ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የት የት ነው የማይደረገው? ለሚለው ጥያቄ "ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር፣ አምባሰል፣ ደጋዳሞት" እና የመሳሰሉት ምርጫ የማይደረግባቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።
በተያያዘ ስድስት ፓርቲዎች ከዘንድሮው ምርጫ ከውድድር ውጭ በመሆናቸው የሚወዳደሩት ደግሞ 42 ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።
ከውድድሩ ውጭ የሆኑት ፓርቲዎች 3ቱ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ፦
• ስምረት፣
• ቃንጪ ሀቂ
• ትንሳዔ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ቀሪዎቹ ፦
• የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣
• የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ)፣
• የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) መሆናቸውን ተናግረዋል።
Seledadotio

10 days ago