(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጣሊያን ሁለት የኢቦላ ተጠርጣሪዎች ተገኙ፡፡ በኡጋንዳ የእርዳታ ሰራተኛ የነበሩ ሁለት ጣሊያናዊያን ሚላን ከተማ ውስጥ በኢቦላ ተጠርጥረው ሆስፒታል መግባታቸው ተዘገበ፡፡ የ30 አመት እድሜ ያለው ወንድና የ31 አመቷ ሴት ከኡጋንዳ ወደአገራቸው የተመለሱት በአዲስ አበባ በኩል አድርገው መሆኑ ተገልጿል፡፡ ሚላን በደረሱበት ወቅት ከፍተኛ ትኩሳት፣ ማስመለስና ነስር ስለታየባቸው ሆስፒታል ገብተው በኳራንቲን ውስጥ እንደሚገኙ አንድ የጣሊያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 900 መድረሱን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 101 ያህሉ በሽታው እንዳለባቸው የተረጋገጠ መሆኑንም አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል በኡጋንዳ ዛሬ በኢቦላ የተያዙ 2 ሰዎች የተገኙ ሲሆን ይህም በአገሪቱ ውስጥ በበሽታው የተያዙትን ቁጥር 7 አድርሶታል፡፡

11 days ago