Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ናሚቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እርዳታ ጠየቀች፡፡ የናሚቢያ መንግስት ብሄራዊ አየር መንገዱን መልሶ ለማዋቀር የኢትዮጵያ አየር መንገድን እርዳታ መጠየቁ ተዘገበ፡፡ ይህንን ጥያቄ ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቴክኒክ አዋጪነት ጥናት መጀመሩም ተገልጿል፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው ለፎርቹን ጋዜጣ ሲናገሩ ‹‹በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተናል፡፡

ይሁንና የመጨረሻ ውሳኔያችንን በጥናት ውጤቱ ላይ የተመሰረተ ይሆናል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም እንዲህ አይነት ሌሎች የጥምረት ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው መሆኑን ጠቅሰው ከሁለት ሌሎች ስማቸውን ካልጠቀሷቸው አገራት ጋር ንግግር እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የናሚቢያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ በ2021 በኪሳራ ምክንያት ስራ ያቆመ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚደረገው ንግግር የሚሳካ ከሆነ በሁለቱ አየር መንዶች ጥምረት ድጋሚ ወደበረራ የሚመለስ ይሆናል፡፡

12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.