(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ዋይት ሀውስ ውጭ ባለው አካባቢ በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ የከፈተ አንድ ግለሰብ መገደሉን የዩናይትድ ስቴትስ ሲክሬት ሰርቪስ አረጋገጠ።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ መሰረት፣ ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰዓት (6:00 p.m) ጥቂት ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ በ17ኛው ጎዳና እና ፔንሲልቬንያ አቬኑ አካባቢ አንድ ግለሰብ ከቦርሳው ውስጥ የጦር መሳሪያ በማውጣት መተኮስ ጀምሯል። በዚህ ጊዜ የሲክሬት ሰርቪስ ፖሊሶች አጸፋዊ ተኩስ በመክፈት ተጠርጣሪውን የመቱት ሲሆን፣ ግለሰቡ ወደ አካባቢው ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል። በዚሁ የተኩስ ልውውጥ ወቅት በአካባቢው የነበረ አንድ አላፊ መንገደኛም በጥይት መመታቱ ታውቋል።
በጥቃቱ በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም። ክስተቱ ሲፈጠር ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሀውስ ውስጥ የነበሩ ቢሆንም፣ በእርሳቸውም ሆነ በሌሎች ጥበቃ በሚደረግላቸው ግለሰቦች እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ የለም። በወቅቱ በስፍራው የነበሩ ጋዜጠኞች ተከታታይ የተኩስ ድምጽ መስማታቸውን ተከትሎ፣ የሲክሬት ሰርቪስ አባላት በፍጥነት ወደ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጫ ክፍል ያስገቧቸው ሲሆን ዋይት ሀውስም ለተወሰነ ጊዜ የደህንነት እገዳ ተጥሎበት ቆይቷል። ይህ እገዳ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ተነስቷል።
ለሲቢኤስ ኒውስ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአጠቃላይ ከ15 እስከ 30 የሚደርሱ ጥይቶች ተተኩሰዋል። የታጠቀው ግለሰብ ወደ ሲክሬት ሰርቪስ ወኪሎች በመጠጋት ተኩስ ቢከፍትም ሳይሳካለት ቀርቶ የአጸፋ እርምጃ ተወስዶበታል።
ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጠረው፣ የዋይት ሀውስ የጋዜጠኞች ማህበር እራት ግብዣ ላይ ተመሳሳይ የተኩስ ጥቃት ከተፈጸመ ከአንድ ወር በኋላ መሆኑ ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል። ክስተቱ በነበረበት ወቅት በዋይት ሀውስ ውስጥ ከነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኩል እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም።

13 days ago