Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹በዚህ አመት ብቻ ሩሲያ 145,000 ወታደሮቿን አጥታለች›› ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በያዝነው የፈረንጆች አመት ማለትም በ20206 ብቻ ሩሲያ 145,000 ወታደሮቿን ማጣቷን ሲገልፁ ከእነዚህ መካከል ወደ86,000 ያህሉ የተገደሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ በዛሬው እለት ከጦር ሀይል ዋና አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲሪስኪ ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንን ቁጥር የጠሩ ሲሆን በተጨማሪም ቢያንስ 59,000 ወታደሮች በፅኑ መቁሰላቸውንና 800 ደግሞ ምርኮኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

የዩክሬይን ወታደሮች በሩሲያ ላይ የሚያደርጉትን ዘመቻ ቀጥለው በወታደሮች ላይ ብቻም ሳይሆን በቁሳቁሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ያስታወቁት ዘለንስኪ በተለይ ከሩሲያ ጋር በሚዋሰነው ሱሚ ግዛት ከፍተኛ ድል መቀዳጀታቸውን ገልፀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹በድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ሱሚ ግዛት የፈለግነውን ግብ አሳክተናል›› ብለዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ይህ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ በሩሲያ ወታደሮች ላይ የደረሰው ጉዳት 1,353,860 መሆኑን ጠቅሰው በትላንትናው እለት ብቻ 800 ወታደሮች መገደላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቢቢሲ ሩሲያ አገልግሎት አደረኩት ባለው ማጣራት ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ የሞቱት የሩሲያ ወታደሮች ቁጥር 217,808 መሆኑን ገልጿል፡፡ በተያያዘ ዜና ዘለንስኪ በዛሬው እለት በሩሲያ ውስጥ 700 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት በአንድ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገልፀዋል፡፡ በኤክስ ገፃቸው ላይም ‹‹አሁን ጦርነቱን ወደሩሲያ ውስጥ እየከተትነው ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው›› ብለዋል፡፡

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.