Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የእሁዱ የአርሰናል የመጨረሻ ግጥሚያ ትኬት ዋጋ ጣራ ላይ ወጣ፡፡ የፊታችን እሁድ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ግጥሚያውን ያደርጋል፡፡ በዚህ ጨዋታ ማጠቃለያ ላይ የክለቡ አምበል ማርቲን ኦዲጋርድ ዋንጫውን ሲያነሳ ለማየት የጓጉ የአርሰናል ቀንደኛ ደጋፊዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይሁንና ለዚህ በደቡባዊ ለንደን ለሚከናወነው ጨዋታ የተዘጋጀው 25,000 የመግቢያ ትኬት ተሸጦ ካለቀ ሰነባብቷል፡፡

ዘሚረር ጋዜጣ እንደዘገበው የአርሰናል ደጋፊዎች ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በስታዲየም ተገኝተው ለመመልከት ያላቸውን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የዚህ ጨዋታ ትኬት ጣራ ላይ ወጥቷል፡፡ ትኬቶቹ አስቀድመው በማለቃቸው አሁን ለገበያ እየቀረቡ ያሉት የገዙትን ትኬት በሚሸጡ የኦን ላይን ድረገፆች ላይ ብቻ ነው፡፡ እንደዘገባው ፉትቦል ትኬትስ ዶትኮም ላይ የመግቢያ ትኬቱ እስከ 33,000 ፓውንድ ተተምኖለታል፡፡ ይህ ክብር ትሪቢዩን ቦታ ላይ ለመቀመጥ የሚያስችል ትኬት መሆኑንም አስረድቷል፡፡

በሌላ በኩል ቲኮምቦ ዶት ኮም ደግሞ በስታዲየሙ ውስጥ በአርሰናል ደጋፊዎች መቀመጫ ላይ ለሚገኝ ትኬት ከ10,000 ፓውንድ በላይ ዋጋ ማውጣቱንና እየሸጠም እንደሚገኝ ዘገባው ገልጿል፡፡ ለዚህ ለእሁዱ ጨዋታ በድረገፆች ገበያ ርካሽ የሚባለው ትኬት ዋጋ 1300 ፓውንድ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው ይህም በክሪስታን ፓላስ ደጋፊዎች በኩል ለመቀመጥ የሚያስችል ነው ብሏል፡፡

16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.